አሊ መሃመድ፣ ሙዚቃ ያቀርባል በስም "አሊ ቢራ"፣ ኢትዮጵያዊ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ዘመናዊ የኦሮምኛ ዘፈን ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል። የአሊ የመድረክ ስም "ቢራ" የተወሰደው ለመጀመሪያ ጊዜ አሊ መድረክ ላይ ካቀረበው ዘፈን፣ "ቢራ ዳ ባሬ"።
አሊ ቢራ በመስከረም ፲፭፣ ፲፱፻፵ ዓ.ም (September 26, 1947) በድሬዳዋ ከተማ ተወለድ። በህጻንነቱ የተለያዩ የአገር ውስጥ እና አለም አወፍ ሙዚቃዎችን እያደመጠ ያደገው አሊ ቢራ ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ እና ለቤተሰቦቹ በማንጎራጎር ነበር የሙዚቃ ህይወቱን የጀመረው። በድሬደዋ ውስጥ ብዙ ቋንቋዎች መኖር ያልገደበው አሊ በአረብኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሃደርኛ እና ሶማሊኛ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር።[1]
ከዛም በ14 አመት አሊ "አፍራን ቃሎ" የተባለ የኦሮሞን ሙዚቃ ለማስተዋወቅ አላማ ያደረገ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድን ተቀላቀለ። በቡድኑ ውስጥ ሌላ አሊ የተባለ ልጅ በመኖሩ ሁለቱን ለመለየት መጀመሪያ ከሚያዜመው "ቢራ ዳ ባሬ" ዘፈን ወስደው "አሊ ቢራ" የሚለውን ሰም ተሰጠው። ከዛም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የተለያዩ ባንዶች ውስጥ የተጫወተው አሊ ቢራ በ፲፻፱፻፸፮ ዓ.ም ከስዊድናዊ ዲፕሎማት ባለቤቱ ጋር ከኢትዮጲያ ወጥቱአል።
በ ዘፈኖቹ የኦሮሞን ባህል በ ደንብ አስተዋውቋል።ኒዲ መን ኢንዴማ የተባለው ዘፈኑ ተወዳጅ ነበር።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |