አምስተርዳም

አምስተርዳም በይፋ (በሕግ) ከ1806 ዓ.ም. ጀምሮ የነዘርላንድ ዋና ከተማ ሆኗል። ሆኖም የነዘርላንድ መንግሥት መቀመጫ በተግባር በደን ሃግ ከተማ ቆይቷል።

በዚህ ሥፍራ መንደር ከ1267 ዓ.ም. ጀምሮ ይዘገባል፤ ስሙም «አምስተለርዳም» ማለት «የአምስተል ወንዝ ገደብ» ተባለ። ወንዙም ከጥንታዊ ሆላንድኛ /አመሰተለ/ «ውሃ ሠፈር» ተሰየመ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 737,900 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 52°21′ ሰሜን ኬክሮስ እና 04°54′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።