አሹር-ዱጉል ከ1678 እስከ 1672 ዓክልበ. ('ኡልትራ አጭሩ' አቆጣጠር) የአሦር ንጉሥ ነበረ።
የአሦር ነገሥታት ዝርዝር የተባለው ሰነድ እንደሚለው፣ ለ፮ ዓመታት ከ1 እሽመ-ዳጋን ቀጥሎ ነገሠ። ስለ አሹር ዱጉል በተጨማሪ እንዲህ ይተርካል፦ «አሹር-ዱጉል ዲቃላ ልጅ ነበረ፣ የዙፋን ማዕረግ አልነበረውም። በአሹር-ዱጉል ዘመን መጀመርያ፣ 6 ሌሎች «ዲቃላ» የተባሉ ጣውንት ነገሥታት ተነሡ፦ አሹር-አፕላ-ኢዲ፣ ናሲር-ሲን፣ ሲን-ናሚር፣ ኢፕቂ-ኢሽታር፣ አዳድ-ሳሉሉ እና አዳሲ ናቸው።»
ከነዚህ ስድስት በላይ፣ በሌላ መዝገብ ዘንድ ሁለት ሌሎች፣ ሙት-አሽኩር (የእሽመ-ዳጋን ልጅ)፣ እና ሪሙ-... ከእሽመ-ዳጋን በኋላ ይዘርዝራል እንጂ ሌሎቹን አይጠቅስም። ከዚህ በላይ በዚህ ወቅት የባቢሎን (የሃሙራቢ) አገረ ገዥ ፑዙር-ሲን ንጉሡን አሲኑም (የሻምሺ-አዳድ ልጅ-ልጅ) አሞራዊ ስለ ነበር ከዙፋኑ እንዳባረረው በማለት አስቀረጸ። ስለዚህ በተጠቅላላ በነዚህ ፮ ዓመታት ምናልባት ፲ ሰዎች ለአሦር ዙፋን ይወዳደሩ ነበር።
የአሹር-ዱጉል ተከታይ በዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰው አዳሲ ልጅ ቤሉ-ባኒ ይባላል። ስለዚህ ያ አዳሲ እንደ አዲሱ አሦራዊ ሥርወ መንግሥት መስራች ይቆጠራል።
የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[1]
ቀዳሚው 1 እሽመ-ዳጋን |
የአሦር ንጉሥ | ተከታይ ቤሉ-ባኒ |