አቅም (Energy) በፊዚክስ ጥናት ሲተረጎም ያንድ ሰው፣ እንስሳ፣ ቁስ፣ ስራ የመሰራት ችሎታ ወይም ለውጥ የማምጣት ችሎታ ማለት ነው። አቅም የሚለካው በጁል (Jules) ነው።
ሳይንሳዊ አቅም በሁለት ይክፈላል
ከላይ እንዳየነው ሁለት አይነት የአቅም አይነቶች አሉ። በነዚህ ስር የሚተዳደሩ ሌሎች አይነቶችም አሉ። ለምሳሌ የ"ኮረንቲ አቅም"፣ የ"ማግኔት አቅም"፣ የ"ድምጽ አቅም"፣ ወዘተ.. ነገር ግን አንዱ አይነት አቅም ወደ ሌላ አቅም ሲቀየር ወይም አይጨምርም ወይም ደግሞ አይቀንስም። የአቅሙ መጠን ምንግዜም አንድ አይነት ነው። በሌላ ቋንቋ፦
ምንጊዜም አቅም አይፈጠርምም አይጠፋምም።
በዚህ ጊዜ ሲጀመርና ሲያልቅ ያለው አቅም እኩል ሆኖ ይገኛል። ይኽውም 50 ጁል ነው ማለት ነው።
በአሁኑ ዘመን ሳይንቲስቶች አንድን ቁስ አካል ወደ አቅም በኑክልያር መበታተን እና ኑክሊያር መገጣጠም መለወጥ እንደሚቻል ደርሰውበታል። በዚህ ምክንያት የአቅም አይጠፋም ህጉ ይህን ጉዳይ ለማስተናገድ ሲባል የቁስና አቅም አይጠፋም ህግ ብለውታል።
ከብዙ በጥቂቱ ...
ከላይ እንደተገለጸው አቅም ይለካል። ይህም በቁጥር ይተመናል። የአቅም መለኪያ ዩኒት ጁል (J) ይባላል። አንድ ጁል ከአንድ ኒውተን ሜትር (1Nm) ወይም ( 1 kg m2 s−2) ጋር እኩል ነው።