አባላ አባያ

አባላ አባያ
Abbala Abbaayaa
ወረዳ
በአባላ አባያ አባያ ሀይቅ ዳርቻ
ሀገር ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
ዞን ዎላይታ
ርዕሰ ከተማ አባላ ፓራቾ
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 56,812

አባላ አባያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በዎላይታ የሚገኝ ወረዳ ነው። ወረዳው 16 የቀበሌ አስተዳደሮችን ያቀፈ ሲሆን ከነዚህም 13ቱ ገጠር 3ቱ ደግሞ ከተማ ናቸው። በ6°38′ N ኬክሮስ እና 37° 42′ E ኬንትሮስ መካከል ተቀምጦ ከአዲስ አበባ በደቡብ 419 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ወረዳው የተቋቋመው እኤአ በ2019 ከአካባቢው ወረዳዎች ነው። [1] አባላ አባያ በደቡብ በኩል በአባያ ሀይቅ[2] በምዕራብ በሁምቦ ወረዳ፣ በሰሜን በሶዶ ዙሪያ ወረዳ፣ በምስራቅ በሆቢቻ ወረዳ ይዋሰናል። የዚህ ወረዳ የአስተዳደር ማዕከል አባላ ፓራቾ ከተማ ነው።

የህዝብ ብዛት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዚህ ወረዳ አጠቃላይ ህዝብ 56,812 አካባቢ ነው። ከዚህም በወረዳው 27,627 አባወራዎች ያሉ ሲሆኑ ከነዚህም 16,981 ወንድ እና 10,646 ሴት አባወራዎች ናቸው። [3]

  1. ^ "Abala Abaya woreda". Archived from the original on 2023-06-10. በ2024-06-23 የተወሰደ.
  2. ^ "direction to Abala Abaya district". Archived from the original on 2021-09-08. በ2024-06-23 የተወሰደ.
  3. ^ "Assessing climate change-induced poverty of mixed crop-livestock smallholders in Wolaita zone". Research in Globalization (ScienceDirect) 7. https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/S2590051X23000485.