አባታችን ሆይ (ግዕዝ፦ አቡነ ዘበሰማያት) ወይም የጌታ ጸሎት በማቴዎስ ወንጌል 6 እና በሉቃስ ወንጌል 11 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው። ጸሎት የግል መሆኑን ካስረዳ በኋላ፥ ጸሎት ግን በገሃድ ስትፈልጉ፥ እግዜር የምትፈልጉትን ገና ስላወቀ፥ እንዲህ ብላችሁ ጸለዩ በማለት አስተማራቸው። በማቴዎስ ወንጌል 6፦
በሉቃስ ወንጌል 11 ከማቴዎስ ትንሽ ይለያል፦
በአብያተ ክርስቲያናት በጋራ በአማርኛ ሲጸለይ ከጥቃቅን ልዩነቶች ጋራ እንዲህ ነው፦
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፣ ትምጻእ መንግሥትከ ፣ወይኩን ፈቃድከ ፣ በከመ በሰማይ ፣ከማሁ በምድር፣ ሲሳየነ፣ዘለለ ዕለትነ፣ሃበነ ዮም። ኅድግ ለነ፣አበሳነ ወጌጋየነ፣ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፣ ኣላ አድኅነነ ወባልሐነ፣እምኩሉ እኩይ፣ እስመ ዚኣከ፣ይእቲ መንግሥት፣ኃይል ወስብሐት፣ ለዓለመ ዓለም፣አሜን።
በሰላመ፣ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፣
ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
ድንግል ብኅሊናኪ ፣ወድንግል በሥጋኪ።
እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ። ቡርክት አንቲ እምአንስት፣ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ። ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ። ሰአሊ ወጸልዪ ምሕረት በእንቲኣነ፣ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
በአማርኛ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ፥ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ። በሀሳብሽ ድንግል ነሽ ፤ በሥጋሽም ድንግል ነሽ አሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘነድ ለዘለዓለሙ አሜን። (የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ፥ ፳፮ - ፶፰።)
የእግዚአብሔር አብ ጸጋ ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን። (፪ኛ ጢሞቴዎስ ምዕ ፩ ቁ ፪።)