አንኮበር

አንኮበር
የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ግቢ
ከፍታ ፪ሺ፬፻፷፭ ሜትር (፰ሺ፰፯ ጫማ)
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ ፪ሺህ ፪፻፹፰
አንኮበር is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አንኮበር

9°34′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°54′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


አንኮበር፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች።

አንኮበር ከዐፄ ይኵኖ አምላክ (፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም) ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት አገልግላለች። ዐፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻፵፬ ዓ/ም የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት ይነገራል። አስቲት ኪዳነ ምሕረት የርሳቸው ትክል ናት። ጦረኛዉ ዓፄ አምደ ጽዮን በ፲፫፻፴፭ ዓ/ም አዳልን ለማስገበር የዐማራን፣ የዳሞትን፣ የጐዣምን ሠራዊት ይዘው አንኮበር ሠፈሩ።ለ፬ ወራት ያህል እስከ ዘይላበርበራ ድረስ በመዝለቅ ድል አድርገው አስገብረውታል።

ዐፄ ልብነ ድንግል (፲፭፻፰-፲፭፻፵ ዓ/ም) ደግሞ በተሻለ ሁኔታ በቦለድ የባለወልድን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ጀምረው እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ ለማድረግ የሸዋ ስርወ-መንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓ/ም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ ፲፰፻፹፩ ዓ.ም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሥር መሠረቱ የረር | እንጦጦ እስከዞረበትና በኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ የምትታወቀው አንኮበር ለአምስት የሸዋ ነገሥታት በማእከልነት አገልግላለች።

አንኮበር የሸዋ ነገሥታት ቋሚ መናኸሪያ ለመሆን የበቃችው ከመርድ አዝማች አምኀየሱስ ዘመነ መንግሥት ሲሆን በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላዶ ሥልጣን በያዙት በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በይበልጥ ተስፋፍታ ነበር። ንጉሡ የእጅ ባለሙያዎችን በከፍተኛ ደረጃ ያበረታቱ ስለነበር፣ በርካታ የእደ ጥበብ ሥራዎች ይከናወኑባት ነበር። በቤተ መንግሥት የሚተዳደሩ ከሺ በላይ አናጺዎችና ግንበኞች በተለይም ባሩድ ቀማሚዎች፣ የጦር መሣሪያ ሠራተኞችና አንጥረኞች በወቅቱ ነበሩባት።

የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዐልጋ ወራሽ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ተተክተው ፰ ዓሙታት ያህል እንደገዙ ሸዋ በዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት ተወረረ። የቴዎድሮስ ሠራዊት አንኮበር ከተማ ግቢው ቅጥሩ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሹማምንቱ የግቢውን ቤተ መንግሥቱን አቃጥለውታል። ዓፄ ቴዎድሮስም በቦታው ድንኳን ጥለው ጥቂት ቀናት ቆይተው የራሳቸውን ወኪል ሾመው ተመልሰዋል። ጥቂት ቆይቶ የሸዋ መኳንንት በአቤቶ ሰይፉ ሣህለ ሥላሴ መሪነት የዓፄ ቴዎድሮስን ተወካይ በዛብህን አባረው ግቢዉን ሲይዙ ዓፄ ቴዎድሮስ ለሁተኛ ጊዜ ወደ ሸዋ ዘምተዉ በተካሄደው ከፍተኛ ጦርነት አንኮበር ክፉኛ መጐዳቷን መረጃዎች ይገልፃሉ። ተዘርፋለች፥ተቃጥላለች።

የ፲፩ ዓመቱ ምኒልክና የሸዋ መኳንንት በግዞት ወደ ጎንደር ተወስደዋል። ምንይሊክ በዓፄ ቴዎድሮስ እጅ በእስራት ከነበሩበት መቅደላ አምልጠው ሲመለሱ አንኮበር እንደገና ተቋቁማ የጥንት ማዕረጓ ተመልሷል።

ዛሬ በአንኮበር ከዓፄ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽ በተጨማሪ በተለያዩ ዘመናት የተሠሩ አምስት አብያተ ክርስቲያናትና ዘመናዊ የጎብኚዎች መቀበያ ይገኛሉ። እነሱም፦

ንጉሥ ምኒልክ እና ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም የጋብቻ ሥነ ስርዓታቸውን ሲፈጽሙ ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉበት የአንኮበር መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን። ይህ ቤተ ክርስቲያን በ፲፯፻፸፪ ዓ/ም ሥራው ቢጀመርም የተፈጸመው በንጉሥ ኃይለ መለኮት፲፰፻፵፮ ዓ/ም ነው።

  • የአማራ ብሔራዊ ክልል፤ ባህል፣ ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ፤ “የአማራ ክልል የቱሪስት መስህብ ሃብቶች (አጭር ቅኝት)”፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት (፲፱፻፺፩ ዓ/ም)