አይን (ሥነ አካል)

Eye
የሰው ልጅ አይን.
ኮምፓውንድ አይን የአንታርክቲ ቅሪል

አይንብርሃንን መኖር የሚያሳውቅ የስሜት ህዋስ ነው። ይህንንም ተግባር የሚፈጽመው አሱ ላይ ያረፈውን ብርሃን ወደ ኮርንቲና ኬሚካል በመቀየር ያንን መልእክት በነርቮቻችን አድርጎ ወደ አንጎላችን በማሻገር ነው። ብዙ ህይወት ያላቸው ነገሮች አይን አላቸው ነገር ግን የሁሉም አይን አንድ አይነት ሃይል ወይም ተፈጥሮ የለውም። ለምሳሌ የጥቃቅን እንስሶች አይን እንደሰው ልጅ አይን አካባቢያቸውን በሚገባ ለይተው እንዲያዩ ሳይሆን የሚረዳቸው እንዴው ለወጉ የብርሃንን መኖር ወይም አለመኖር ብቻ እንዲያውቁ ነው የሚረዳቸው። ሌሎች ታላላቅ እንስሳት በጣም የተወሳሰብ አይን ሲኖራቸው አይናቸውም ከአዕምሮአቸው ጋር የሚያያዙባቸው የነርቭ ክፍሎች እንዲሁ የተወሳሰቡ ናቸው። ባጠቃላይ 96% የሚሆን በምድራችን የሚኖሩ እንስሶች የተወሳሰቡ አይኖች ሲኖሩዋቸው እነዚህ የተወሳሰቡ አይኖች በ10 ዓይነት ለይቶ የማየት ችሎታ ይከፈላሉ።