ኢርካብ-ዳሙ ከ2115-2109 ዓክልበ. ግድም የኤብላ ንጉሥ ነበር። የኤብላ ጽላቶች የተባሉት ሰነዶች ክምችት ይህን ዘመን ይጠቅላል። የማሪ ንጉሥ ኢብሉል-ኢል ከኤብላ ብዙ መሬት በጦርነት ይዞ ነበር። በኢርካብ-ዳሙ መጀመርያው ዓመት ግን የኤብላ ሻለቃ ኤና-ዳጋን ኢብሉል-ኢልን አሸንፎ አዲስ ንጉሥ ኒዚ በማሪ ዙፋን አነሣ። በቅርብ ጊዜ ግን ኤና-ዳጋን እራሱ የማሪን ንጉሥነት ማዕረግ ያዘ።
ኢርካብ-ዳሙ ደግሞ ከሐማዚ ንጉሥ ዚዚ ጋራ ስምምነት እንደ ተዋዋለ ይዘገባል።
ቀዳሚው ኢግሪሽ-ሐላብ |
የኤብላ ንጉሥ 2115-2109 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኢሻር-ዳሙ |