ኢኩኑም የአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1842-1828 አካባቢ ገዛ። የኢሉሹማ ልጅና የወንድሙ የ 1 ኤሪሹም ተከታይ ይባላል።
በሃቲ የነበሩት ካሩም (የንግድ ጣቢያዎች) አስቀጠለ፤ እንዲሁም አንዳንድ ቤተ መቅደስ ወይም አምባ እንዳሠራ ከጽላቶቹ ይታወቃል።
የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና ብዙ ጊዜ የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።
ለ1841 ዓክልበ.፣ አንዱ የሊሙ ዝርዝር በ«ኢዲን-ሲን፤ የሹሊ ወንድም» ፈንታ «ሹሊ፤ የሻሊማሁ ልጅ» ይጻፋል። መግለጫው አንድ ሊሙ በዓመቱ ውስጥ አርፎ በወንድሙ ተተካ ሳይሆን አይቀርም።[1]
ቀዳሚው 1 ኤሪሹም |
የአሹር ገዥ 1842-1828 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 1 ሳርጎን |