ኤምፒ3 ድምፅን ወይም ዘፈንን በኮምፒውተር ላይ ማስቀመጫ ፎርማት ነው። ቴክኖሎጂው ከተፈጠረ ፳ ዓመት ገደማ ይሆነዋል። በብዛት በዘፈን ማጫዎቻዎች እንዲሁም ለድረ ገጽ ራዲዮዎች፣ ለፖድካስት ማጫዎቻዎች ይጠቅማል።
ዋና ጥቅሙና ተወዳጅ ያደረገው ነገር ብዙ የድምፅ መረጃን፣ዘፈን በጣም ጥቂት በሆነ ቦታ ለማስቀመጥ ያስችላል። ለምሳሌ 20(፳) ገደማ የሚሆን ሲዲ ከኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት ውጭ የተዘጋጀ ሲዲ ኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት በመጠቀም በአንድ ሲዲ ልናዘጋጀው እንችላለን።ይህ ማለት ወደ 200(፪፻) ዘፈኖችን በአንድ ሲዲ ማስቀመጥና ማጫዎት ማለት ነው።
የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች ሙዚቃውን የሚያከማችበት የተለያየ ዘዴ አለው። አይነቶቹም የሚከተሉት ናቸው።