እምቧይ (Solanum incanum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ቊጥቋጣም ዕጽ አንድ ሜትር ይደርሳል።
ይህ ተክል ባጠቃላይ መርዛም ሲሆን፣ በማስለመድ በኩል የባዚንጀን (Solanum melongena) አያት ሆነ።
በኢትዮጵያ ግዛት በሰፊው የተስፋፋ ነው። ባጠቃላይ በተፈጀ መስክ ወይም መንገድ ዳር በጣም ተራ ነው።
ድቡልቡል ፍሬዎቹ ደማቅ ብርቱካን ሲሆኑ ልጆች ለመቅሰም ይፈተናሉ፤ ስለዚህ በልጆች መመረዝ ይደርስባቸዋል። ጥርሱም በዘለቄታ የተበለዘ፣ የተጎዳ ይሆንባቸዋል።
ከሽንት ጋር በመቃላቀል ፍሬው በቆዳ ፋቂ ፍብሪካ ውስጥ፣ ወይም ጨብጡ ለማከም ተጠቅሟል።[1]
ሥሩም ለአሚባ በሽታ ወይም ለእባብ ነከስ ይኘካል።[2]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |