እርካብቱም የያምኻድ ንጉሥ ምናልባት ከ1587 እስከ 1575 ዓክልበ. አካባቢ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) በዋና ከተማው ሐላብ ነገሠ።
እርካብቱም በተለይ በአላላኽ ከተገኙት ጽላቶች ይታወቃል። የአላላኽ ንጉሥ አሚታኩም ለእርካብቱም ተገዥ ሲሆን የጋራ ጠረፋቸውን ያስተካክል ነበር። ወደ ኤፍራጥስ ምሥራቅ በናሽታርቢ አገር ባመጹበት ሑራውያን ላይ ዘመተ።
እርካብቱም ደግሞ ከ«ሃቢሩ» ወገንና ከአለቃቸው «ሰሙመ» ጋር ስምምነት አደረገ። «ሃቢሩ» የሚለው ስያሜ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የሚታይ ይሄ ነው።
የእርካብቱም ስም ደግሞ በአንድ ኬጥኛ ጽላት ላይ ተገኝቷል።
ቀዳሚው ንቅሚ-ኤፑሕ |
የያምኻድ ንጉሥ 1587 – 1575 ዓክልበ. ግ. |
ተከታይ 2 ሃሙራቢ |