እንዶድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
በመላው ኢትዮጵያ ግዛት በተለይም በወይና ደጋ ተራ ነው።
በአፍሪካና በማዳጋስካር፣ በተለይም በኢትዮጵያና ኤርትራ ይገኛል።
ሥሩ ወይም ቅጠሉ ተደቅቆ በውሃ ለቁርባ ወይም ወፍ በሽታ ይጠጣል። የሥሩ መረቅ ለጨብጡ ያከማል። በአነስተኛ መጠን ካልሆነ ሊገድል ይችላል።[1] የወንድ እንዶድ ሥር ተድቅቆ በውሃ ደግሞ ውሻ በሽታን ለማከም ይጠጣል።[2] ወይም እንዲህ በጤፍ ቂጣ ይበላል።[3]
የእንዶድ ቅጠል ጭማቂ ለእከክ መቀባቱ፣ ወይም ለሆድ ትል መጠጣቱ ተዝግቧል።[4] የፍሬውም ለጥፍ ለቁስል ይለጠፋል።
ፍሬው ተደርቆ ተድቅቆ ለሳሙና መጠቀሙ ጥንታዊ ልማድ ነው። ደግሞ አሣን በማደንዘዝ በአጥማጆች ተጠቅሟል።
በ1956 ዓም፣ አንድ የኢትዮጵያ ሳይንቲስት ዶ/ር አክሊሉ ለማ የእንዶድ ሳሙና ዛጎል ለበስን እንደሚያጥፋ ለይተው አገኙ። የቢልሃርዝያ በሽታ በዛጎል ለበስ ስለሚፈጠር፣ ቢልሃርዝያን በመከላከል ከፍ ያለ ሚና አገኝቷል። ዶክተሩም የእንዶድ ማዕከል ኣቋቁመዋል በዚህም ዕውቅናን እትርፋል። ሌሎችንም አስቸጋሪ ቀንድ አውጦች ወይም ተባዮች ለማጥፋት ስለሚችል እንዶድ በስሜን አሜሪካ ትኩረትና ፓቴንቶች አገኝቷል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |