እንጎችት Stephania abyssinica ወይም ያይጥ ሐረግ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ሌሎች ስሞች በአንዳንድ ምንጭ «ክብ ቅጠል» እና «እጸ ኢየሱስ» ተገኝተዋል።
«መሬት ለመሬት የሚሳብ ሐረጉ ቅጠሉ ክብነት ያለው።» - አቢሲኒካ
የመላው እንጎችት ተክል ውጥ የላም ደዌ ጡት፣ በሰውም ቂጥኝ እና ቁርባ ለማከም ይጠቀማል ከዚህም በተጨማሪ ምስጢረ ጥበብ የሚገልፅበት መንገድ አለው ።[1]
በሌላ ጥናት እንደ ተዝገበ፣ የቅጠልና የአገዳው ጭማቂ ለሆድ ቁርጠት መጠጣት፣ የአገዳው ለጥፍ ለኪንታሮት መለጠፍ፣ በተደቀቀው ቅጠል መታጠብ ለ«ግርፍታ» (ትኩሳት፣ ራስ ምታት) ማከም ይጠቀሳል።[2]
የሥሩ ዱቄት በጤፍ ተጋግሮ ለቁርጥማት፣ ሪህ፣ አንጓ ብግነት ይበላል።[3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |