እንፍራዝ | |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 9,162 (2005 ተገምቷል) |
እንፍራዝ ወይም እምፍራዝ በሌላ ስም፣ ጉባኤ ወይም ጉዛራ በመባል የሚታወቅ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ክፍል ነው። ይህ አካባቢ በባህርዳር-ጎንደር መንገድ ላይ የሚገኝ፣ ከጣና ሐይቅ ስሜን ምስራቅ ላይ ያለው ከተማ ነው። እንፍራዝ በታሪክ ቀደምት ተጠቅሶ የሚገኘው በ14ኛው ክፍለ ዘመን፣ ገብረ እያሱ የተሰኘው የእውስጣጢዎስ ደቀመዝሙር በአካባቢው ገዳም በመመስረቱ ነው[1] ። ግራኝ አህመድ በ1543 የክሪስታቮ ደጋማን ሰራዊት ድል ካደረገ በኋላ የክረምት ወራትን ለማሳልፍ እዚህ እንደሰፈረ ይጠቀሳል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |