ኪልቅያ

ኪልቅያ በደቡብ-ምሥራቅ አናቶሊያ

ኪልቅያ (ግሪክኛ፡- Κιλικία /ኪሊኪያ/፣ አሦርኛ፡- ሒላኩ፣ ሒሊኩ) በጥንት ደቡብ-ምሥራቅ አናቶሊያ (የአሁኑ ቱርክ አገር) የተገኘ አውራጃ ነበረ።

ኬጢያውያን መንግሥት ዘመን አገሩ «ኪዙዋትና» ይባል ነበር። ከዚያ በኋላ ሆሜር የኪልቅያ ሰዎች የትሮያ ጓደኞች እንደ ነበሩ ይጽፋል።