ዋቅላሚ

ዋቅላሚዎች

የቃሉ መሰረታዊ አመጣጥ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቅላሚ[1] የሚለው ቃል የተገኘው “ውሃ” እና “አቅላሚ” ከተሰኙ ሁለት የአማርኛ ቃላት ሲሆን “Algae” ለሚለው የላቲን ቃል የአማርኛ አቻ ቃል ነው። ስያሜው እንደሚያመለክተው በዚህ መደብ ስር ያሉ ፍጡራን ውሃን የማቅለም ባህርይ አላቸው።

ነጠላቁጥር የሆነውና አልጋ "alga" የተሰኘው ቃል በላቲን የባህር አረም "sea weed" ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛም ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡[2] የባህር አረም 'seaweed'የሚለው ቃል በጥንታዊ ግሪክ ፋይኮስ φῦκος (phŷkos) ይባል የነበረ ሲሆን ትርጓሜውም የባህር አረም(ምናልባትም ቀይ ዋቅላሚ) ወይም ከቀይ ዋቅላሚ የሚገኝ ቀለም ማለት እንደነበር ይታመናል፡፡ የዋቅላሚ ጥናት ፋይኮሎጂ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አልጎሎጂ የተሰኘው ቃል ከአገልግሎት ውጭ እየሆነ የመጣ ቃል ነው።[3] [4]

The kelp forest exhibit at the Monterey Bay Aquarium: A three-dimensional, multicellular thallus
በሞንተሬይ ቤይ መርእይ ገንዳ ውስጥ የሚገኝ የከልፕ ጫካ ኤግዝቢት

ዋቅላሚ የሚለው ቃል ከተለያዩ ስርወዘራዊ ቡድኖች የተገኙ እና በተለያዩ የሥርዓተ ምደባ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ሕይወት ያላቸው ፍጡራንን የሚወክል ሰፊ ቡድን ነው። በአጠቃላይ ዋቅላሚዎች ስንል እያልን ያለነው፦ በአብዛኛው እውነተኛ ስር፣ግንድ፣ ቅጠል እና ሥርአተሸንዳ የሌላቸው ባለ ቀላል የመራቢያ መዋቅር የሆኑ እና ምግብሰሪ የሆኑ የውሃውስጥ ዕፅዋትመሰል ፍጡራንን ነው። በመላው ዓለም ማለትም፦ በባሕር፣ በጨው አልባ ዉሃማ አካላት እና እርጥበታማ የየብስ ክፍሎች ተሰራጭተው ይገኛሉ። አብዛኛዎቹ ሚክሮስኮፓዊ ሲሆኑ ጥቂቶች ግን በጣም ግዙፎች ናቸው። ለምሳሌ አንዳንድ የባሕር ውስጥ አረሞች (seaweeds) እስከ ፶ ሜትር ያህል ሊረዝሙ ይችላሉ። [5]

በውሃ ላይ የሚንሳፈፉ ዋቅላሚዎች ፋይቶፕላንክተን ይባላሉ፡፡[6] ዋቅላሚዎች ብዙ የመራቢያ ስልቶች አሏቸው፤ ክለኤ ቁርሰት ከተሰኘው ተራ ኢ-ጾታዊ የመራቢያ ስልት ውስብስብ እስከሆኑ ጾታዊ የመራቢያ ስልቶች ይታይባቸዋል፡፡[7]

ስርዓተ ምደባ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአለምአቀፉ የእፅዋት ስያሜ ኮድ ኮሚቴ ለዋቅላሚ ስርዓተምደባ የሚያገለግሉ የተወሰኑ ቅጥያዎችን ለመጠቀም ምክረሃሳብ አቅርቧል፡፡ እነዚህም ቅጥያዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

-ፋይታ(-phyta)ለክፍለሰፍን፣ ፋይሲያይ(-phyceae) ለመደብ፣ ፋይሲዲያይ(-phycideae)ለንዑስ መደብ፣ አለስ (-ales) ለክፍለመደብ፣ ኢናለስ(-inales)ለንዑስ ክፍለመደብ፣ አሲያይ(-aceae)ለአስተኔ፣ ኦይዲስ (-oidease)ለንዑስ አስተኔ፣ የግሪክ መሰረት ያለው ስያሜ ለ ወገን፣ የላቲን መሰረት ያለው ስያሜ ለዝርያ ናቸው፡፡ ከ 800 በላይ የዋቅላሚ ወገኖች ሲኖሩ እያንዳንዱ የዋቅላሚ ወገን በስሩ የተለያዩ ዝርያዎችን ይይዛል።

ለመጀመሪያ ደረጃ ምደባ መሰረት የሆኑ የዋቅላሚዎች ባህሪያት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዋቅላሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምደባ የተወሰኑ የስነቅርፅ ገፅታዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከነዚህ ገፅታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-

(ሀ) የህዋስ የቀለም ተዋፅኦ፣ (ለ) የተከማቸ ምግብ ኬሚካላዊ ተፈጥሮ፣ (ሐ)የተንቀሳቃሽ ህዋሳት ልምጭት አይነት፣ ቁጥር፣ የመጋጠሚያ ነጥብ እና አንፃራዊ ርዝመት (መ)የህዋስ ግንብ መዋቅር እና

(ሠ) በህዋሱ ውስጥ በትክክል የተደራጀ ኒውክለስ የመኖርና ያለመኖር ሁኔታ ወይም በተለየ ሁኔታ ጉልህ የሆነ የህዋስ መዋቅር ናቸው።

ዋና ዋናዎቹ የዋቅላሚ ስርወዘራዊ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው[8] [9]

አረንጓዴ ዋቅላሚዎች (chlorophyta)

ባልጩት ዋቅላሚዎች (Bacillariophyta)

ወርቃማ ዋቅላሚዎች (Chrysophyta)

ኢዩግሊኖፋይታ (Euglenophyta)

ዳይኖፍላጅላታ (Dinoflagellata)

ቡናማ ዋቅላሚዎች (Phaeophyta)

ቀይ ዋቅላሚዎች (Rhodophyta)

ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች (Cyanobacteria)

ዋቅላሚዎች አስገራሚ የስነቅርፅ ተለያይነት የሚታይባቸው ፍጥረቶች ናቸው፡፡ ስነ ቅርፃቸው ላይ በመመስረት ዋቅላሚዎች ፡- አንድህዋሴ ዋቅላሚዎች፣ ኩይዋሳዊ ዋቅላሚዎች፣ዘሃዊ ዋቅላሚዎች፣ መቆ ዋቅላሚዎች እና ዥንቃዊ ዋቅላሚዎች[10] በሚባሉ መደቦች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡

1.    አንድ-ህዋሴ ዋቅላሚዎች (Unicellular algae)፦ ህዋስግንብ ያላቸው የማይንቀሳቀሱ ነጠላ ህዋሳት ወይም በሚያጣብቅ ነገር ውስጥ ያሉ የማይንቀሳቀሱ ህዋሳት ናቸው።

2.   ኩይዋሳዊ ዋቅላሚዎች(Colonial algae)፦ የትናንሽ ተንቀሳቃሽ ህዋሳት መደበኛ ቡድኖች።

3.   ዘሃዊ ዋቅላሚዎች(filamentous algae)፦ እንደ ጨሌ ገመድ ሰንሰለት ሰርተው የተደረደሩ ህዋሳት ህዋሳት ናቸው። እንደ ስፓይሮጋይራ ያሉ ዝርያዎች ቅርንጫፍ ይሌላቸው ሲሆኑ እንደ ስቲጎኔማ ያሉት ደግሞ ቅርንጫፍ አላቸው።

4.    መቆ ዋቅላሚዎች(Siphonaceous algae)፦ መቆ ዋቅላሚዎች የሚባሉት በአንድ ህዋስ ውስጥ ብዙ ኒውክለሶች ያሏቸው ፣ ማለትም በህዋስ ግንቦች ባልተከፋፈለ አንድ ቤተህዋስ ውስጥ ብዙ ኒውክለሶች የሚገኙበት የዋቅላሚ አይነት ነው፡፡

5.    ዥንቃዊ ዋቅላሚዎች(Parenchymatous algae)፦ ህብረህዋስ መሰል የሆነ ብቃይ አካል ያላቸው ዋቅላሚዎች ናቸው። ለምሳሌ በብዙ ሜትር የሚለካ ርዝመት ያለው ማክሮሲስቲስ ከዥንቃዊ ዋቅላሚዎች አንዱ ነው።

ዋቅላሚዎቸ በውሃ አካላት ውስጥ በስፋት ይገኛሉ፤ በየብስ ላይም በተለመደ መልኩ ይገኛሉ እንዲሁም በበረዶ አካላት ላይና ባልተለመዱ ቦታዎች ይገኛሉ። የባሕር ውስጥ አረሞች የሚባሉት ከ100 ሜትር በላይ ጥልቀት በሌላቸው የውሃ አካላት ውስጥ ይገኛሉ። ነገርግን እንደ ናቪኩላ ፔናታ ያሉ ዝርያዎች እስከ 360 ሜትር ጥልቀት ድረስ እንደሚገኙ ተመዝግቧል።[11] የተለያዩ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለውሃ ስነ ምህዳር ወሳኝ ሚና አላቸው። በውሃማ አካላት ውስጥ ተንሳፍፈው የሚገኙ ዋቅላሚዎች (ፋይቶፕላንክተኖች) ለአብዛኛው የባህር ውስጥ የምግብ ሰንሰለት መሰረት ሆነው ያገለግላሉ።በሳይንቲስቶች ግምት መሰረት በከባቢ አየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው የሚመረተው የብርሃን አስተፃምሮ በሚያካሂዱ ዋቅላሚዎች ነው፡፡[12]

በተፈጥሮ የሚያድጉ ዋቅላሚዎች በጣም ጠቃሚ የምግብ ምንጭ ናቸው። በተለይ በእስያ አህጉር በአንዳንዶች እጅግ በጣም ጠቃሚ ተብለው የተለዩ አሉ። [13] ቫይታሚን A, B1, B2, B3, B6, እና ቪታሚን C ይዘው ይገኛሉ። በአዮዲን፣ ፖታሲየም፣ ብረት፣ማግኒዥየም እና ካልስየም የበለፀጉ ናቸው። [14] በተጨማሪም ለገበያ የሚመረቱ ደቂቅዋቅላሚዎቸ ሲያኖባክቴሪያዎችን ጨምሮ እንደ ስፓይሩሊና እና ክሎሬላ ያሉት ለስርዓተ-ምግብ ማሟያ ተብለው ይሸጣሉ። በቤታ ካሮቲን ከበለፀገው ዱናሌላ የቪታሚን C ማሟያ ይመረታል። [15]

ዋቅላሚዎች በብዙ አገራት ብሔራዊ ምግብ ናቸው። በቻይና ፋት ቾይን ጨምሮ ከ70 በላይ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለብግብነት ይውላሉ። በጃፓን ኖሪ እና አውኖሪን ጨምሮ ከ20 በላይ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለምግብነት ይውላሉ።[16] በአየርላንድ ደልስ፣ በቺሊ ኮካዩዮ ለምግብነት የሚውሉ የዋቅላሚ አይነቶች ናቸው። [17] በዌልስ የሌቨርዳቦ ወይም ባረ ለውር የሚባለውን ምግብ ለማዘጋጀት ሌቨር የሚባል ዋቅላሚ ጥቅም ላይ ይውላል፤ በኮሪያ ደግሞ ጂም የሚሰኝ ዋቅላሚ ለምግብነት ያግለግላል። በስኮትላንድ፣ አየርላንድ፣ ግሪንላንድ እና አይስላንድ የባህር ሰላጣ(sea lettuces) እና ባደርሎክ የሰላጣ ግብዓቶች ናቸው። በአሁኑ ሰዓት ዋቅላሚዎች የአለምን የምግብ ችግር ለመፍታት እምቅ አቅም ያላቸው አማራጭ መሆናቸው ከግምት ውስጥ እየገባ ነው። [18] [19][20]

ለምግብ ዝግጅት የሚያገለግሉ ሁለት ታዋቂ የዋቅላሚ ዝርያዎች አሉ፡

  • ክሎሬላ፦ ይህ የዋቅላሚ ዝርያ በጨው እልባ የውሃ አካላት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአረንጓቀፉ ውስጥ ለፎቶሲንተሲስ የሚያግለግሉ ቀለማት አሉት። በብረት፣ ዚንክ፣ ማግኒዥየም፣ ቪታሚንB2

እና ኦሜጋ-3 ፋቲአሲድ የበለፀገ ነው። በተጨማሪም ሰውነታችን በራሱ ያማያመርታቸውን ዘጠኙንም አሚኖ አሲዶች ይዞ ይገኛል።[21]

  • ስፓይሩሊና፦ የሲያኖባክቴረያ ዝርያ ሲሆን በፕሮቲን ይዘቱ በ10% ከክሎሬላ የላቀ ነው፤ እንዲሁም ከክሎሬላ የተሻለ የመዳብ እና የቪታሚን B1 ይዘት አለው።[22]

አጋር ከቀይ ዋቅላሚ የሚዘጋጅ ወፍሮ የመጋገር ባህሪይ ያለው ልዩቁስ(substance) ሲሆን በንግዱ አለም ከፍተኛ ተፈላጊነት አለው። [23] አብዛኛዎቹ ደቂቅ አካላት አጋርን ማብላላት የማይችሉ በመሆናቸው በላዩ ላይ ባክቴሪያ እና ፈንገስ ለማሳደግ ምቹ ማሳደጊያ ነው።

አርጂኒክ አሲድ ወይም አርጂኔት ከቡናማ ዋቅላሚዎች የሚገኝ ውህድ ነው። ጥቅሞቹ ለምግብ ማወፈሪያ ከመዋል አንስቶ ለቁስል መሸፈኛነት ጭምር ነው። በባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ አገልግሎት አለው። በኒውሜክሲኮ አርጂኔት ለማዘጋጀት እና ለአበሎኒ ምግብነት በኣመት ከ100,000 እስከ 170,000 ቶን የሚደርስ ማክሮሲስቲስ ይመረታል። [24] [25]

የሀይል ምንጭ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለወደፊቱ ተወዳዳሪ ለመሆን እና በየጊዜው ከሚቀያየረው የሀገርውስጥ ፖሊሲ ባለፈ ራስን ለመቻል የባዮፊውል ዋጋ ከተፈጥሮ ነዳጅ ዋጋ ማንስ አለበት ካልሆነም እኩል መሆን ይኖርበታል። እዚህ ጋ ዋቅላሚን መሰረት ያደረጉ የነዳጅ ውጤቶች ትልቅ ተስፋ ሰጪ ቦታ ይይዛሉ፤ ይህም በቀጥታ የሚያያዘው በተወሰነ ቦታ ላይ በአንድ አመት ውስጥዋ ቅላሚዎች ባላቸው ከፍተኛ ምርት የመስጠት አቅም ላይ ነው። [26] [27]

ለብክለት ቁጥጥር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ፍሳሽ ቆሻሻ በዋቅላሚዎች ሊታከም ይችላል፤ ይህም ለፍሳሽ ቆሻሻ ማከሚያ የሚውሉ ከፍተኛ መጠን ያላቸው መርዛማ ኬሚካሎችን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሔ ነው። [28]
  • ዋቅላሚዎች ከእርሻ በጎርፍ ታጥበው የሚሄዱ ማዳበሪያዎችን ለማጥመድ ይጠቅማሉ፤ በቀጣይነት በማዳበሪያ የበለጸገውን ዋቅላሚ እንደማዳበሪያ መጠቀም ይቻላል።
  • የውሃ ማቆሪያዎችን ወይም ኩሬዎችን በዋቅላሚ አማካኝነት ማጽዳት ይቻላል፤ ይህም የሚሆነው ( algae scrubber) ወይም ( turf scrubber) የሚባል መሳርያ ባለብት ዋቅላሚዎች በውሃ ውስጥ ያለውን ንጥረነገር እንዲመጡ በማድርግ ነው።

የግብርና ምርምር አገልግሎት ተመራማሪዎች በጎርፍ ታጥቦ ከሚሄደው ናይትሮጅን ከ60–90%የሚሆነው እንዲሁም ከ70–100% የሚሆነው ፎስፈረስ በ(algal turf scrubber(ATS)) አማካኝነት ከፍግ ፍሳሾች ውስጥ መሰብሰብ እንደሚቻል ደርሰውበታል።[29]

  1. ^ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት /እንግሊዝኛ - አማርኛ/ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዴሚ ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ታህሳስ፣ 1989 አዲስ አበባ። Science and Technology Dictionary (English - Amharic), Academy of Ethiopian Languages, Artistic Printing Press, 1996, ] Addis Ababa
  2. ^ "alga, algae". Webster's Third New International Dictionary of the English Language Unabridged with Seven Language Dictionary. Vol. 1. Encyclopædia Britannica, Inc. 1986.
  3. ^ Cheyne, Thomas Kelly; Black, John Sutherland (1902). Encyclopædia biblica: A critical dictionary of the literary, political and religious history, the archæology, geography, and natural history of the Bible. Macmillan Company. p. 3525.
  4. ^ Lee, Robert Edward, ed. (2008), "Basic characteristics of the algae", Phycology (4 ed.), Cambridge: Cambridge University Press, pp. 3–30, doi:10.1017/CBO9780511812897.002, ISBN 978-1-107-79688-1, retrieved 13 September 2023
  5. ^ https://www.lenntech.com/eutrophication-water-bodies/algae.htm#ixzz6aq4M83Vi
  6. ^ https://en.wikipedia.org/w/index.php?title=Algae&oldid=1178697513
  7. ^ Smithsonian National Museum of Natural History; Department of Botany. . Retrieved 25 August 2010
  8. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2007-08-08. በ2022-06-02 የተወሰደ.
  9. ^ http://en.wikipedia.org/wiki/Algae
  10. ^ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት /እንግሊዝኛ - አማርኛ/ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዴሚ ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ታህሳስ፣ 1989 አዲስ አበባ። Science and Technology Dictionary (English - Amharic), Academy of Ethiopian Languages, Artistic Printing Press, 1996, ] Addis Ababa
  11. ^ Round (1981), p. 176.
  12. ^ https://atlas-scientific.com/blog/does-algae-produce-oxygen/
  13. ^ Jung, Frederich; Kruger-Genge, Anne; Kupper, J.-H.; Waldeck, P (April 2019). "Spirulina platensis, a super food?". ResearchGate. 5: 43. Retrieved 21 December 2020.
  14. ^ Simoons, Frederick J. (1991). "6, Seaweeds and Other Algae". Food in China: A Cultural and Historical Inquiry. CRC Press. pp. 179–190. ISBN 978-0-936923-29-1.
  15. ^ Morton, Steve L. "Modern Uses of Cultivated Algae". Ethnobotanical Leaflets. Southern Illinois University Carbondale. Archived from the original on 23 December 2008. Retrieved 26 December 2008.
  16. ^ Mondragón, Jennifer; Mondragón, Jeff (2003). Seaweeds of the Pacific Coast. Monterey, California: Sea Challengers Publications. ISBN 978-0-930118-29-7.
  17. ^ Durvillaea antarctica (Chamisso) Hariot". AlgaeBase.
  18. ^ "How marine algae could help feed the world". World Economic Forum. Retrieved 21 June 2018.
  19. ^ "One solution to global hunger could be at the bottom of the ocean". World Economic Forum. Retrieved 21 June 2018.
  20. ^ "Algae: Pond Scum or Food of the Future?". HowStuffWorks. 12 June 2018. Retrieved 21 June 2018.
  21. ^ Rani, Komal; Sandal, Nidi; Sahoo, PK (2018). "A comprehensive review on chlorella- its composition, health benefits, market and regulatory scenario" (PDF). The Pharma Innovation Journal. 7 (7): 585. Archived (PDF) from the original on 9 October 2022. Retrieved 21 December 2020.
  22. ^ Bantilan, C., MS, RD, CD. (2020, July 15). What's the difference between chlorella and spirulina? Healthline. https://www.healthline.com/nutrition/chlorella-spirulina
  23. ^ Lewis, J. G.; Stanley, N. F.; Guist, G. G. (1988). "9. Commercial production of algal hydrocolloides". In Lembi, C. A.; Waaland, J. R. (eds.). Algae and Human Affairs. Cambridge University Press. ISBN 978-0-521-32115-0.
  24. ^ "Macrocystis C. Agardh 1820: 46". AlgaeBase. Archived from the original on 4 January 2009. Retrieved 28 December 2008.
  25. ^ "Secondary Products of Brown Algae". Algae Research. Smithsonian National Museum of Natural History. Archived from the original on 13 April 2009. Retrieved 29 December 2008.
  26. ^ Yang, Z. K.; Niu, Y. F.; Ma, Y. H.; Xue, J.; Zhang, M. H.; Yang, W. D.; Liu, J. S.; Lu, S. H.; Guan, Y.; Li, H. Y. (4 May 2013). "Molecular and cellular mechanisms of neutral lipid accumulation in diatom following nitrogen deprivation". Biotechnology for Biofuels. 6 (1):
  27. ^ Wijffels, René H.; Barbosa, Maria J. (2010). "An Outlook on Microalgal Biofuels". Science. 329 (5993): 796–799. Bibcode:2010Sci...329..796W. doi:10.1126/science.1189003. PMID 20705853. S2CID 206526311.
  28. ^ "Re-imagining algae". Australian Broadcasting Corporation. 12 October 2016. Archived from the original on 2 February 2017. Retrieved 26 January 2017.
  29. ^ "Algae: A Mean, Green Cleaning Machine". USDA Agricultural Research Service. 7 May 2010. Archived from the original on 19 October 2010.