ዓርብ የሳምንቱ ስድስተኛ ቀን ሲሆን ከሐሙስ በኋላ ከቅዳሜ በፊት ይገኛል።
ዓርብ በኃይማኖትም ዘንድ ለየት ያለ ዋጋ ካላቸው ቀኖች አንዱ ነው። በክርስቲያኖች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ በመሆኑ ለየት ያለ ክብደት ይሰጠዋል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ከዘመነ ፋሲካ ውጪ ዓርብ የጾም ቀን ነው። ለሙስሊም ወንዶችም ዓርብ ቀትር ላይ በመስጊድ ተገኝቶ የጋራ ጸሎት ማድረግ ግዴታ ነው። በመስጊድ መሰባሰብ ግዴታ አይሁን እንጂ ለሴቶችም የጸሎት ቀን ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |