ዓፄ እስክንድር ወይም ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ (ከ፲፬፻፸፩ እስከ ፲፬፻፹፯ ዓ.ም. ነገሡ) ከዓፄ በእደ ማርያም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ።[1]
አጼ እስክንድር የአጼ በዕደ ማርያም ልጅ ፡ የአጼ ናዖድ ደግሞ ወንድም ናቸው። ለሃይማኖኖታቸው በማድላት መንግሥታቸውን ትተው የመነኑ ታላቅ አባት ናቸው። ብዙ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ጌታም ተአምራትን እንዲሰሩ እንደሙሴ የላካቸው ፍጹም አማኝ እና ባህታዊ አባት ነበሩ። የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ግንቦት 11 ቀን ነው። አጼ እስክንድር አዋልድ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡ ደቂቀ እስጢፋኖስም በመቃወም ይታወቃሉ። በቀጣይነት ታሪካቸው በተሟላ ሁኔታ ለመጻፍ ተጨማሪ ጽሁፎችን እናካትታለን።
[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- ^ ሓሪ አትክንስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ገፅ 14