ዚካ ትኩሳት | |
---|---|
Classification and external resources | |
![]() አሌክስስ ሳልቫዶር ዚካ ቫይረስ | |
ICD-10 | U06.9 Code change from 21 December 2015 |
ICD-9 | 066.3 |
ዚካ ትኩሳት፣ እንዲሁም የዚካ ቫይረስ በሽታተብሎ የሚጠራው፣ በዚካ ቫይረስ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ [1] ምልክቶቹ ከ ከቆላ ንዳድ ጋር ይመሳሰላሉ፡፡ [1] ከ (60–80%) የሚሆነው ታማሚ ምልክት የለውም፡፡ [2] ምልክቶቹ በሚከሰቱ ጊዜ በአብዛኛው በትኩሳት፣ የአይን መቅላት, የመገጣጠሚያ ህመም፣ ራስምታትና በቆዳ ሽፍታስር ይጠቃለላሉ፡፡ [3][1] በአጠቃላይ ምልክቶቹ ቀለል ያሉና ቆይታቸውም ከአምስት ቀናት ያነሰ ነው፡፡ [4] በሽታው በ2015 በጀመረ ጊዜ የደረሰ ሞት አልነበረም፡፡[2] በሽታው ከ ከጡንቻ መዛል ህመም ጋር ግንኙነት አለው፡፡ [2]
የዚካ ትኩሳት በዋነኛነት የሚሰራጨው በ ቢንቢ ንክሻ ሲሆን እሱም ከ ኤደስ ስር ይመደባል፡፡ [4] በግብረስጋ ግንኙነትና በደም ንክኪም የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ [4] በሽታው ከ በፅንስ ወቅት ከእናት-ወደ-ልጅ የሚተላለፍ ተሰራጭቶ በሚወለደው ልጅ ላይ ከመደበኛው ያነሰ የራስ ቅል እንዲሀኖረው ሊያደርግ ይችላል፡፡ [1][2] አንድ ሰው ሲታመም በምርመራ የቫይረሱን አር.ኤን.ኤለማወቅ የደም፣ ሽንት ወይም ምራቅ ናሙና ተወስዶ ይመረመራል፡፡ [4][1]
በሽታው በተከሰተበት አካባቢ የቢንቢ ንክሻውን ለመቀነስ የቅድመ መከላል መደረግ ይኖርበታል፡፡ [4] ጥረቶቹም ነፍሳት ማባረሪያ፣ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል በልብስ መሸፈን፣ አጎበር፣ የረጋ ውሃ ለቢንቢ መራቢያ ምቹ ስለሚሆን እሱን ማድረቅ፡፡ [1] ውጤታማ የሆነ ክትባት አልተገኘለትም፡፡ [4] በ2015 የብራዚል የጤና ተጠሪዎች እንሚመክሩት ለማርገዝ እቅድ ላላቸው ወላጆችና እርጉዝ የሆነች ሴት በሽታው ስርጭት በስፋት ወደታየበት ቦታ እንዳትሄድ ይመክራሉ፡፡ [5][4] ለህመሙ የተለየ የሕክምና አይነት ባይኖርም የትኩሳት ማስታገሻ መድሐኒት ህመሙ በሚኖር ጊዜ ለመርት ያስችላል፡፡ [4] ሆስፒታል መመዝገብ የሚያስፈልገው አልፎ አልፎ ነው፡፡ [2]
ለበሽታው መነሻ የሚሆነው ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየው በ 1947 ነው፡፡ [6] በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በ በማክሮኔዢያ ፌደራል ስቴት በሚገኙ ህዝቦች መሀል በ2007 ላይ ነው፡፡ [4] በ2016 በ አሜሪካ ክልል ባሉ ሀያ ሀገራት ላይ ተከስቷል፡፡ [4] እንዲሁም በአፍሪካ፣ እስያና ፓስፊክ አካባቢ መከሰቱ ታውቋል፡፡ [1] በ2015 በብራዚል በጀመረው ስርጭት፣ የ አለም ጤና ድርጅት የ አለማቀፋዊ የአስቸኳይ ጊዜ የማህበረሰብ ጤና ትኩረት አውጇል፡፡ [7]