የሜዳ ቀይ ሕንዳውያን እጅ ምልክት ቋንቋ (Plains Indian Sign Language ወይም PISL) በዩናይትድ ስቴትስ ታላቅ ሜዳዎች ላይ በኖሩት በስሜን አሜሪካ ኗሪዎች (ቀይ ሕንዳውያን) የተፈጠረ የእጅ መነጋገሪያ ነበረ።
በአሜሪካና በካናዳ በሮኪ ተራሮች ምሥራቅና በሚሲሲፒ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው አገር በብዛት ሰፊ ሜዳዎች ነው። በነዚህ ላይ ብዙ የተለያዩ የአገር ኗሪ ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ጎሽን እያደኑ ይመላለሱ ነበር። እነዚህም አገሮች ሁሉ የየራሳቸው ቋንቋ ነበራቸው። ከዚህ በላይ ልሳናታቸው ባልተዛመዱ ቤተሠቦች ውስጥ ስለሆነ እርስ በርስ በመነጋገር ትንሽ ተቸገሩ። በዚህ ምክንያት ጎሣዎቹ ሁሉ የሚጠቀሙበት የእጅ መነጋገሪያ ቋንቋ ተለማና ተስፋፋ።
ይህ ዘይቤ በአውሮፓውያን መጀመርያ በ1533 ዓ.ም. በስፓንያዊው አለቃ ኮሮናዶ ታየ። በ1877 ዓ.ም.፣ ቋንቋውን የቻሉት ኗሪዎች ቁጥር በ110፣000 ተገመተ። እነዚህ ከአልጎንኲን ቤተሠብ የሲክሲካ (ብላክፉት)፣ የጺጺስታ (ሻየን)፣ የሂኖኖኧይኖ (አራፓሆ) ተነጋሪዎች፣ እንዲሁም የካወጉ (ካዮዋ) እና የላኮታ (ሱ) ተነጋሪዎች ይጠቀልል ነበር።[1] ነገር ግን በ1960ዎቹ 'ከዚህ ቁጥር በጣም ጥቂት ከመቶ' ቀሩ።[1] ዛሬም ጥቂት PISL የሚችሉ አሉ።
PISL ልዩ ስዋሰው አለው።