?የምድር እምቧይ | ||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
የምድር እምቧይ
| ||||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||
|
የምድር እምቧይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
የዚህ ኪያር ፍሬው በጣም መርዛም ነው አይበላም።
የምድር እምቧይ በውነት እምቧይ አይደለም፤ የኪያር ዘመድ ነው።
የሮማይስጥ ስሙ Cucumis prophetarum ማለት «የነቢያት ኪያር» ሲሆን፣ ይህም ከአረብኛው «የኒቢዩ ኪያር» ወይም «የውሻዎች ኪያር» ከመባሉ ነው።
ሌላ ተመሳሳይ የኪያር ወገን ዝርያ Cucumis ficifolius ደግሞ «የምድር እምቧይ» ተብሏል።
ከዚህም በላይ የምድር እምቧይ ቢጫው ፍሬ እንደ ሌላ ዱባ ዝርያ የበረሃ ቅል Citrullus colocynthis ትንሽ ይመስላል፤ እሱም (Citrullus colocynthus) ደግሞ አንዳንዴ «የምድር እምቧይ» ተብሏል።
በመስክ ይታያል። በከፊል ደረቅ አየር ይገኛል።
ፍሬው ለልጆች ኳስ ተጠቅሟል እንጂ መርዛም ስለ ሆነ አይበላም።[1]
በአንድ ጥናት ዘንድ፣ ሥሩ (C. ficifolius) የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት ተዘገበ። ሥሩን መብላት ለእባብ ነከስ፣ ወይም ለ«ሞኝ ባገኝ» (አበባ ሰንጋ)። ሥሩን ጭማቂውንም መኘካት ለሆድ ቁርጠት ወይም ለትኩሳት («ምች»)። ሥሩ ተድቅቆ እንደ ለጥፍ ለ«ቁስል መርዝ» (የቁስል ልክፈት)። ሥሩ በቅቤ እንድ ለጥፍ ለችፌ። ሥሩም ከአንዳንድ ሌሎች ተክሎች ጋር ሌሎችንም ጥቅሞች አሉት።[2]
በተጨማሪ ጥናት፣ የሥሩ (C. ficifolius) መኘካት ደግሞ ለቁርባ፣ አኖሬክሲያ፣ ለወላድ ምጥ ያከማል፤ የሥሩም ዱቄት በማር ለማጅራት ገትር ይበላል፣ በጤፍ ቂጣ ለውሻ በሽታ ይበላል፤ በ[[ወተት] ወይም ኑግ ለወፍ በሽታ በጥዋት ይጠጣል፤ ወይም ለነስር የሥሩ ጭማቂ ወደ አፍንጫ ማስገባት ነው።[3]
እንደገና በሌላ ጥናት፣ የመላው C. ficifolius ተክል መረቅ ትልን ለማስወጣት፣ ወይም የከብቶች ተቅማጥ ለማከም፣ ለመጠጣት ይሰጣል።[4]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |