የሞንቲ ሖል እድል ጥያቄ በዕድል ጥናት ውስጥ በቅርብ ጊዜ ታዋቂነትን ያተረፈ ጥያቄ ነው። ጥያቄው እንዲህ ነው፡
በዘልማድ እንግዲህ መኪናውን የማሸነፍ እድሉ በሁለቱም የተዘጉ በሮች ዘንዳ አንድ አይነት ይመስላል። ብዙ ሰወች እንደሚያስቡት፣ ተጫዋቹ ሃሳቡን ቀየረ አልቀየረ መኪናውን የማግኘት እድሉ አይጨምርምም አይቀንስም። ነገር ግን እውነተኛ የሂሳብ ጥናት እንደሚያስተውል የተጨዋቹ የማሸነፍ እድል ከ 1/3ኛ ወደ 2/3ኛ ያድጋል፣ ስለሆነም ሃሳቡን መቀየሩ የማሸነፍ ዕድሉን ይጨምርለታል።መኪና
እንግዴህ ተጫዋቹ ከ፫ቱ በሮች አንዱን መምረጡ የማሸነፍ እድሉን 1/3ኛ ያደርገዋል (ማሸነፍ እዚህ ላይ መኪና ማግኘት ማለት ነው)። መኪናው ከሌሎቹ ሁለት በሮች ውስጥ የመሆን እድሉ 2/3ኛ ነው ማለት ነው። ስለሆነም የማሸነፍ እድሉን ከ1/3ኛ ወደ 2/3ኛ ለማሳደግ ምርጫውን በመቀየር ከመረጠው "አንድ" በር ወደ "ሁልቱ" በሮች ማሳደግ ብልህነት ነው። አስተናጋጁ ፍየል ያለበትን ሁለተኛ በር መክፈቱ ተጫዋቹን ለማምታት እንጂ ተጫዋቹ "አንድ በር" ከመምረጥ ይልቅ "ሁለት በር" መምረጡን አያስተባብልም።
1.1 (አጣ): ተጫዋቹ በመጀመሪያ ምርጫው መኪናዋን ቢመርጥ፣ አስተናጋጁ ፍየል ያለበትን በር ያሳያል። እንግዲህ ተጫዋቹ ሃሳቡን ቢቀይር፣ ፍየል ያገኛል።
2. (አሸነፈ) : ተጫዋቹ በመጀመሪያ ምርጫው ፍየል ከመረጠ፣ አስተናጋጁ ሁለተኛውን ፍየል ያሳያል ማለት ነው። ተጫዋቹ ሃሳቡን ቢቀይር፣ መኪና ያገኛል።
3. (አሸነፈ) : ተጫዋቹ በመጀመሪያ ምርጫው ሌላኛዋን ፍየል ከመረጠ፣ አስተናጋጁ አንደኛዋን ፍየል ያሳያል ማለት ነው። ተጫዋቹ ሃሳቡን ቢቀይር፣ መኪና ያገኛል።
ስለሆነም ተጫዋቹ ሃሳቡን ከቀየረ፣ ከ3ቱ ጊዜ ሁለት ጊዜ መኪናዋን ያገኛል (ያሸንፋል)።