የራውንድኸይ ገነት ትርኢት |
|
|
|
ርዕስ በሌላ ቋንቋ | Roundhay Garden Scene |
የተለቀቀበት ዓመት | 1881 ዓም |
ያዘጋጀው ድርጅት | |
ዳይሬክተር | ሉዊ ለ ፕረንስ |
አዘጋጅ | |
ምክትል ዳይሬክተር | |
ጸሐፊ | |
ሙዚቃ | |
ኤዲተር | ሉዊ ለ ፕረንስ |
ተዋንያን | አኒ ሃርትሊ አዶልፍ ለ ፕረንስ ጆሰፍ ውትሊ ሳራ ውትሊ |
የፊልሙ ርዝመት | 2.11 ሴኮንድ |
ሀገር | እንግላንድ |
ወጭ | |
ገቢ | |
ዘውግ | {{{ዘውግ}}} |
የፊልም ኢንዱስትሪ |
የራውንድኸይ ገነት ትርኢት በጥቅምት 5 ቀን 1881 ዓም የተቀረጸ የዓለም መጀመርያው ተንቀሳቃሽ ፊልም እንደ ነበር ይታመናል።[1] ፊልሙን ያቀረጸው የፈረንሳይ ፈጠራ ፈልሳፊ ሉዊ ለ ፕረንስ ሲሆን ቦታው በራውንድኸይ ሰፈር ሊድስ፣ እንግላንድ በጆሰፍና ሳራ ውትሊ ቤት ግቢ «ኦክዉድ ግሬንጅ» ነበር።[2] የውትሊዎች ልጅ ኤልሳቤት የሉዊ ለፕረንስ ሚስት ነበረች፣ አዶልፍም የለፕረንሶች ልጅ ሲሆን በፊልሙ ከጓደኛው አኒ ሃርትሊ አጠገብ ይታያል። እንዳጋጣሚ ወ/ሮ ሳራ ውትሊ ከተቀረጸው 10 ቀን በኋላ አረፉ።[3]
የፊልሙ ርዝመት 2.11 ሴኮንድ ብቻ ሲሆን ከ1881 ዓም ጀምሮ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ወይም ጭፈራ በቀጥታ መመልከት የሚያስችል በመሆኑ ግሩም ነው። ባለድምጽ ፊልም ገና ስላልኖረ ይሄ ድምጽ-የለሽ ፊልም ይባላል።