የቅሌምንጦስ ስነ ጽሑፍ ስለ ክርስትና አጀማመር ከኢየሱስ ክርስቶስ ስብከት ጀምሮ የሚመሰክሩ ታሪካዊ ጽሑፎች ናቸው።
ጸሓፊው እኔ ቅሌምንጦስ ነኝ ቢለንም በዛሬው አውሮጳውያን መምህሮች በኩል የሚጠራጥሩ ስላሉ አንዳንድ «ሐሣዊ-ቅሌምንጦስ» ይሉታል። ቅሌምንጦስም ከኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከስምዖን ጴጥሮስ በኋላ የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳስ (ወይም «ፓፓ») ሀነ።
ታሪኩ እንደሚመሰክረው፣ ቅሌምንጦስ የሮሜ ከተሜ ሲሆን፣ በአንዱ ዓመት በቄሣር ጢባርዮስ ዘመን ውስጥ፣ የሚከተለው ወሬ እስከ ዓለም ዳርቻዎች ድረስ በአፍ ቶሎ ተስፋፋ፦
በዚያው ዓመት ከይሁዳ ወደ ሮሜ የደረሰው ሰው ሁሉ እንዲህ አይነት ወሬ ስለ ደገመው፣ በተለይም በቅንነት እንጂ በጠማማነት እንዳልተናገሩ ስለ መሠላቸው፣ የሮሜ ኗሪዎች ከነቅሌምንጦስ እጅግ ሲገርሙ፣ በዓመቱም ውስጥ ባርናባስ የተባለው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር በሮሜ ደርሶ በአደባባይ ስለክርስቶስ አዋጀ፣ እንዲህ ብሎ፦
ከሮሜ ሕዝብ አንዳንዱ ባርናባስን ቢከራክረው ቅሌምንጦስ ግን ሰምቶት በመከታው ድምጹን አነሣ። ከጊዜ በኋላ ባርናባስ ወደ ይሁዳ ተመለሰና ቅሌምንጦስ ደግሞ በተረፈ ለመረዳት እራሱ ወደ ይሁዳ ተጓዘ። እዚያ ስምዖን ጴጥሮስን አገኝቶ አሁን ከትንሳኤ በኋላ ስለ ሆነ ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ስብከት፣ ስቅለትና ዕርግት ለቅሌምንጦስ አስረዳ።
ከዚያ በኋላ ስምዖን ጴጥሮስ ከሌሎች ሃይማኖታዊ ንቅናቄ መሪዎች በተለይም ከስምዖን ጠንቋዩ ጋር እያከራከረ ቅሌምንጦስ ይሰማል። ይህም ስምዖን በሐዋርያት ሥራ ፰፤፱ የተጠቀሰው ጠንቋይ ሲሆን፣ በነዚህ ጽሑፎች መሠረት ዮሐንስ መጥምቁ ከተገደለ በኋላ (22 ዓ.ም. ግድም) ከሳምራውያን ወገን አንድ ዶሲጤዎስ የተባለ ሐሣዊ መሢህ በፈንታው ተነሥቶ፣ ከዚያ ሳምራዊው ስምዖን ጠንቋዩ በዶሲጤዎስ ፈንታ ተተካ፤ እሱም ሌላ ሐሣዊ መሢህ ሆነ። ሁለቱ ሳምራውያን እኔ መሢህ ነኝ ባዮች ነበሩ ማለቱ ነው። ከዚህ በላይ ስምዖን ጠንቋዩ መረንነትን ያስተምር ነበር።
ቅሌምንጦስ በልጅነቱ በሮሜ ከቤተሠቡ ተለይቶ ነበር፤ ክርስቲያን ከሆነ በኋላ ግን ከጴጥሮስ ጋራ በሜዲቴራኔያን ባህር ዙሪያ ወንጌልን እየሰበኩ በእግዜር ፈቃድ እናቱን፣ ወንድሞቹንና በመጨረሻ አባቱን በሕይወታቸው አገኟቸው።