የተስፋ ቁልፍ

የተስፋ ቁልፍ1924 ዓ.ም. ግድም በጃማይካዊው ሰባኪ ሌናርድ ፒ ሃወል የተጻፈ የራስታፋራይ እንቅስቃሴ ጽሑፍ ነው።

ይሄ ጽሁፍ መጀመርያው «ራስታፋራይ» ሊባል የሚችለው ሰነድ ነው፤ ሃወልም ከቅድመኞቹ የራስታፋራይ ሰባኪዎች መካከል አንዱ ነበር። የጻፈው በብዕር ስም «ጎንግ ጉሩ ማራግ» ሥር ነበር። የጃማይካ ቅኝ አገር ባለሥልጣናት እንደ ረባሽ አሠሩት፣ ምናልባት ታስሮ ሳለ ጽሑፉን ያዘጋጀው ይሆናል።

ብዙዎች ዐረፍተ ነገሮች አስቀድሞ (1918 ዓ.ም) በፊፅ ባልንታይን ፐተርስቡርግ በተጻፈው «የጥቁር ላዕላይነት ንጉሣዊ ጥቅል ብራና» (ሮያል ፓርችሜንት ስክሮል ኦቭ ብላክ ሱፕሬማሲ) ተወስደዋል፤ ለምሳሌ፣ በሁለቱ ሥራዎች ውስጥ «አስቀያሚ ውበት በገሐነም ንግሥት ነች!» የሚለው መፈክር የምዕራባውያንን ሥነ ውበት ሲሳድብ ይገኛል። በ«ንጉሣዊ ጥቅል ብራና» ዘንድ ግን የ«ንጉሥ አልፋ» እና የ«ንግሥት ኦሜጋ» መታወቂያዎች ፊፅ ባልንታይን ፐተርቡርግ እራሱ እና ሚስቱ ሲሆኑ፣ በሃወል ድርሰት ግን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና የእቴጌ መነን መታወቂያዎች መሆናቸውን መጀመርያ ገለጸ።

ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ክርስትና እና ስለ ጃንሆይ ሥራተ ነግሥም ይገልጻል። ጃንሆይ በራሳቸው እግዚአብሔር ወልድ ተመልሰው ስለ ሆኑ አዲስ ሃይማኖት መመሥረት እንደሚያስፈልግ የሚል ጽሑፍ ነው። እነዚህ እምነቶች እስካሁንም ድረስ በራስታፋራይ (ራስተፈሪያውያን) እንቅስቃሴ አማኞች በኩል ተቀብለዋል።

በጽሑፉ ደግሞ ጥቁሮች ከሌሎች ዘሮች ብልጫ አንዳላቸው ይላልና ስለ ነጮች በተለይም ስለ እንግሊዝ ዘር ብዙ ስድቦች ሲኖሩበት፣ ዛሬው ግን ስለ ጃንሆይ እራሳቸው ቃላት እጅግ በማጥናት፡ አብዛኛው ራስታዎች በዘሮች እኩልነት የሚያምኑ ናቸው።

  • ጥቅስ፦ «በንጉሥ አልፋ መዝገበ እውቀት፣ ዓለሞች እንዴት እየተሠሩና በምን ቃታ ላይ መንግሥታት እንደሚቀመጡ ለሁላችን ይገልጻሉ። የትውልዳትን ችሎታዎች ደግሞ ይገልጹልናል።»