የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ከብዙ ቅርሶች ተገኝቷል። ከነዚህ ዋንኛው እራሱ «የአሦር ነገሥታት ዝርዝር» የተባለው ጽሑፍ ነው። ይህ ጽሑፍ ከ3 ቅጂዎች ሲታወቅ፣ ከ2 ሳርጎን አስቀድሞ (ወይም እስከ 730 ዓክልበ. ድረስ) የነገሡትን ነገሥታት ይዘረዝራል። ከ1 ኤሪሹም ጀምሮ ሰነዱ ለያንዳንዱ ንጉሥ የዘመኑን አመታት ቁጥር ይሰጣል። ስለዚህ ዝርዝሩ የተቀናበረው በ2 ሳርጎን ዘመን እንደ ሆነ ይታመናል።
በአሦራዊው መቆጠሪያ፣ እያንዳንዱ አመት በሊሙ (ሹም) ስም ይባል ነበር። ለአንዳንድ ንጉስ ዘመን፣ እነዚህን የአመት ስሞች የሚዘርዝሩ ተጨማሪ ዜና መዋዕሎች ተገኝተዋል። በተለይም በቅርብ ጊዜ (በ1995 ዓ.ም.) በካነሽ ፍርስራሽ (በዛሬው ቱርክ አገር) ከ1 ኤሪሹም እስከ አሹር-ዱጉል ድረስ የነበሩት የአመት ስሞች ተገኝተዋል። የአመት ስም ዝርዝሮች በብዛት ከዋናው የነገሥታት ዝርዝር ጋር ይስማማል። ከሺህ አመት በላይ አሦራውያን የአመቶችን ቁጥር በደንብ ስለ ለዩ፣ እነዚህ ቅርሶች የጥንታዊ ዘመን ታሪክና ዕድሜ መጠን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል።
[በኤብላ ጽላቶች የ«አባርሳል ውል» ትርጉም የአሦር ንጉሥ ቱዲያ ከሆነ፣ ከቱዲያ በፊት የማሪ ንጉሥ ኢብሉል-ኢል አሦርን ገዛ።]
[ከቱዲያ በኋላና ከኡሽፒያ በፊት ያሉት ስሞች በሌላ ምንጭ ባይታወቁም በአካድ ንጉሥ ማኒሽቱሹ ዘመን የአሦር ሻካናካ (ገዥ ወይም ከንቲባ) አዙዙ ከቅርስ ታውቋል፤ እንዲሁም የአሦር ሻካናካ ኢቲቲ በጋሱር (ኑዚ) ላይ ድል አንዳደረገ ይታወቃል።[1]
[የኡር ንጉሥ አማር-ሲን ሻካናካ (አገረ ገዥ) ዛሪቁም ከ፩ ፑዙር-አሹር አስቀድሞ በአሦር እንደ ገዛ ይታሥባል።]
የአሦር ነገሥታት ዝርዝር | ||
የንጉሥ ስም | የአመታት ቁጥር | ነጥቦች |
---|---|---|
1 ኤሪሹም | 30 / 40 (ዝርዝር) 40 (አመት ስሞች) 1881-1842 ዓክልበ. |
«የኢሉሹማ ልጅ»፤ የአሦር መቅደስ እንዳሠራ ተባለ። |
ኢኩኑም | ጽሕፈቱ ጠፍቷል (ዝርዝር) 14 (አመት ስሞች) 1842-1828 ዓክልበ. |
«የኢሉሹማ ልጅ» |
1 ሳርጎን | ጠፍቷል (ዝርዝር) 40 (አመት ስሞች) 1828-1790 ዓክልበ. |
«የኢኩኑም ልጅ» (በአሦርኛ ስሙ «ሻሩ-ኬን» ነበር።) |
2 ፑሹር-አሹር | ጠፍቷል (ዝርዝር) 8 (አመት ስሞች) 1790-1782 ዓክልበ. |
«የሳርጎን ልጅ» |
ናራም-ሲን | ጠፍቷል (ዝርዝር) 54 (አመት ስሞች) 1782-1730 ዓክልበ. |
«የፑዙር-አሹር ልጅ» |
2 ኤሪሹም | ጠፍቷል (ዝርዝር) 10 (አመት ስሞች) 1730-1720 ዓክልበ. |
«የናራም-ሲን ልጅ» |
1 ሻምሺ-አዳድ | 33 (ዝርዝር) 33 (አመት ስሞች) 1720-1688 ዓክልበ. |
«ኢላ-ካብካቢ ልጅ፣ በናራም-ሲን ዘመን ወደ ካርዱንያሽ (ባቢሎን) ሄደ። በ'እብኒ-አዳድ' አመት ስም፣ ሻምሺ-አዳድ ከካርዱንያሽ ወጣ። ኤካላቱምን ይዞ 3 አመት በዚያ ቆየ። በ'አታማር-እሽታር' አመት ስም፣ ሻምሺ-አዳድ ከኤካላቱም ወጣ፣ የናራም-ሲንም ልጅ ኤሪሹም ከዙፋን አባረረውና ያዘው።» እርሱም በተራው በባቢሎን ንጉሥ ተባረረ። |
1 እሽመ-ዳጋን | 40 (ዝርዝር) 11 (አመት ስሞች) 1688-1678 ዓክልበ. |
«የሻምሺ-አዳድ ልጅ» |
አሹር-ዱጉል | 6 (ዝርዝር) 1678-1672 ዓክልበ. |
«ዲቃላ ልጅ፣ የዙፋን ማዕረግ አልነበረውም» |
(የአሹር-ዱጉል ተፎካካሪዎች) | - | «በአሹር-ዱጉል ዘመን መጀመርያ፣ 6 ሌሎች «ዲቃላ» የተባሉ ጣውንት ነገሥታት ተነሡ፦ አሹር-አፕላ-ኢዲ፣ ናሲር-ሲን፣ ሲን-ናሚር፣ ኢፕቂ-ኢሽታር፣ አዳድ-ሳሉሉ እና አዳሲ ናቸው።» በሌላ መዝገብ ዘንድ፣ ሙት-አሽኩር (የእሽመ-ዳጋን ልጅ)፣ ሪሙ-... እና አሲኑም (የሻምሺ-አዳድ ልጅ-ልጅ) ደግሞ በዚህ ወቅት በተፎካካሪነት ተነሡ። |
ቤሉ-ባኒ | 10 (ዝርዝር) 1672-1662 ዓክልበ. |
«የአዳሲ ልጅ» |
ሊባያ | 17 (ዝርዝር) 1662-1645 ዓክልበ. |
«የቤሉ-ባኒ ልጅ» |
1 ሻርማ-አዳድ | 12 (ዝርዝር) 1645-1634 ዓክልበ. |
«የሊባያ ልጅ» |
ኢፕታር-ሲን | 12 (ዝርዝር) 1634-1623 ዓክልበ. |
«የሻርማ-አዳድ ልጅ» |
ባዛያ | 28 (ዝርዝር) 1623-1596 ዓክልበ. |
«የቤሉባኒ ልጅ» |
ሉላያ | 6 (ዝርዝር) 1596-1590 ዓክልበ. |
«ዲቃላ ልጅ» |
ሹ-ኒኑዓ | 14 (ዝርዝር) 1590-1576 ዓክልበ. |
«የባዛያ ልጅ» |
2 ሻርማ-አዳድ | 3 (ዝርዝር) 1576-1573 ዓክልበ. |
«የሹ-ኒኑዓ ልጅ» |
3 ኤሪሹም | 13 (ዝርዝር) 1573-1561 ዓክልበ. |
«የሹ-ኒኑዓ ልጅ» |
2 ሻምሺ-አዳድ | 6 (ዝርዝር) 1561-1555 ዓክልበ. |
«የኤሪሹም ልጅ» |
2 እሽመ-ዳጋን | 16 (ዝርዝር) 1555-1539 ዓክልበ. |
«የሻምሺ-አዳድ ልጅ» |
3 ሻምሺ-አዳድ | 16 (ዝርዝር) 1539-1524 ዓክልበ. |
«የሹ-ኒኑዓ ልጅ (2) ሻርማ-አዳድ ልጅ (ሌላ) እሽመ-ዳጋን ልጅ» |
1 አሹር-ኒራሪ | 26 (ዝርዝር) 1524-1499 ዓክልበ. |
«የእሽመ-ዳጋን ልጅ» |
3 ፑዙር-አሹር | 24 / 14 (ዝርዝር) 1499-1476 ዓክልበ. |
«የአሹር-ኒራሪ ልጅ»; በባቢሎን ንጉሥ 1 ቡርና-ቡርያሽ ዘመን ነገሠ |
1 ኤንሊል-ናሲር | 13 (ዝርዝር) 1476-1463 ዓክልበ. |
«የፑዙር-አሹር ልጅ» |
ኑር-ኢሊ | 12 (ዝርዝር) 1463-1451 ዓክልበ. |
«የኤንሊል-ናሲር ልጅ» |
አሹር-ሻዱኒ | 1 ወር (ዝርዝር) 1451 ዓክልበ. |
«የኑር-ኢሊ ልጅ» |
1 አሹር-ራቢ | (የዝርዝሩ ጽሕፈት ጠፍቷል) 1451-1441 ዓክልበ. |
«የኤንሊል-ናሲር ልጅ፤ በመንፈቅለ መንግሥት ዙፋኑን ያዘ» |
1 አሹር-ናዲን-አሔ | (የዝርዝሩ ጽሕፈት ጠፍቷል) 1441-1431 ዓክልበ. |
«የአሹር-ራቢ ልጅ» |
2 ኤንሊል-ናሲር | 1431-1425 ዓክልበ. | «የእርሱ ወንድም፣ አባረሩት» |
2 አሹር-ኒራሪ | 1425-1418 ዓክልበ. | «የኤንሊል-ናሲር ልጅ» |
አሹር-ቤል-ኒሸሹ | 1418-1409 ዓክልበ. | «የአሹር-ኒራሪ ልጅ» |
አሹር-ረዕም-ኒሸሹ | 1409-1402 ዓክልበ. | «የአሹር-ቤል-ኒሸሹ ልጅ» |
2 አሹር-ናዲን-አሔ | 1402-1392 ዓክልበ. | «የአሹር-ረዕም-ኒሸሹ ልጅ» |
1 ኤሪባ-አዳድ | 1392-1366 ዓክልበ. | «የአሹር-ቤል-ኒሸሹ ልጅ» |
1 አሹር-ኡባሊት | 1366-1331 ዓክልበ. | «የኤሪባ-አዳድ ልጅ» |
ኤንሊል-ኒራሪ | 1331-1321 ዓክልበ. | «የአሹር-ኡባሊት ልጅ» |
አሪክ-ደን-ኢሊ | 1321-1309 ዓክልበ. | «የኤንሊል-ኒራሪ ልጅ» |
1 አዳድ-ኒራሪ | 1309-1278 ዓክልበ. | «የአሪክ-ደን-ኢሊ ልጅ» |
1 ስልማናሶር | 1278-1249 ዓክልበ. | «የአዳድ-ኒራሪ ልጅ»። (በአሦርኛ «ሹልማኑ-አሻረዱ») |
1 ቲኩልቲ-ኒኑርታ | 1249-1213 ዓክልበ. | «የስልማናሶር ልጅ» |
አሹር-ናዲን-አፕሊ | 1213-1209 ዓክልበ. | «የቲኩልቲ-ኒኑርታ ልጅ፣ በአባቱ ዘመን ዙፋኑን ቀማ» |
3 አሹር-ኒራሪ | 1209-1203 ዓክልበ. | «የአሹር-ናዲን-አፕሊ ልጅ» |
ኤንሊል-ኩዱሪ-ኡጹር | 1203-1198 ዓክልበ. | «የቲኩልቲ-ኒኑርታ ልጅ» |
ኒኑርታ-አፒል-ኤኩር | 3 / 13 ዓመት (ዝርዝር) 1198-1186 ዓክልበ. |
«የኢላ-ሐዳ ልጅ፤ የኤሪባ-አዳድ ተወላጅ፣ ወደ ካርዱንያሽ ሄደ፤ ከካርዱንያሽም ወጥቶ ዙፋኑን ቀማ» |
1 አሹር-ዳን | 1186-1140 ዓክልበ. | «የአሹር-ናዲን-አፕሊ ልጅ» |
ኒኑርታ-ቱኩልቲ-አሹር | «አጭር ሰዓት» (ዝርዝር) 1140 ዓክልበ. | «የአሹር-ዳን ልጅ» |
ሙታኪል-ኑስኩ | «አጭር ሰዓት» (ዝርዝር) 1140 ዓክልበ. | «የኒኑርታ-ቱኩልቲ-አሹር ወንድም፣ ከርሱ ጋር ተዋጋና ወደ ካርዱንያሽ ወሰደው» |
1 አሹር-ረሽ-ኢሺ | 1140-1122 ዓክልበ. | «የሙታኪል-ኑስኩ ልጅ» |
1 ቴልጌልቴልፌልሶር | 1122-1083 ዓክልበ. | «የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ» (አሦርኛ፦ ቱኩልቲ-አፒል-ኤሻራ) |
አሻሪድ-አፒል-ኤኩር | 1083-1081 ዓክልበ. | «የቴልጌልቴልፌልሶር ልጅ» |
አሹር-ቤል-ካላ | 1081-1063 ዓክልበ. | «የቴልጌልቴልፌልሶር ልጅ» |
2 ኤሪባ-አዳድ | 1063-1061 ዓክልበ. | «የአሹር-ቤል-ካላ ልጅ» |
4 ሻምሺ-አዳድ | 1061-1057 ዓክልበ. | «የቴልጌልቴልፌልሶር ልጅ፤ ከካርዱንያሽ ወጥቶ ኤሪባ-አዳድን አባረረና ዙፋኑን ቀማ» |
1 አሹር-ናሲር-ፓል | 1057-1038 ዓክልበ. | «የሻምሺ-አዳድ ልጅ» |
2 ስልማናሶር | 1038-1026 ዓክልበ. | «የአሹርናሲርፓል ልጅ» |
4 አሹር-ኒራሪ | 1026-1020 ዓክልበ. | «የስልማናሶር ልጅ» |
2 አሹር-ራቢ | 1020-979 ዓክልበ. | «የአሹርናሲርፓል ልጅ» |
2 አሹር-ረሽ-ኢሺ | 979-974 ዓክልበ. | «የአሹር-ራቢ ልጅ» |
2 ቴልጌልቴልፌልሶር | 974-942 ዓክልበ. | «የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ» |
2 አሹር-ዳን | 942-919 ዓክልበ. | «የቴልጌልቴልፌልሶር ልጅ» |
2 አዳድ-ኒራሪ | 919-898 ዓክልበ. | «የአሹር-ዳን ልጅ» |
2 ቱኩልቲ-ኒኑርታ | 898-891 ዓክልበ. | «የአዳድ-ኒራሪ ልጅ» |
2 አሹር-ናሲር-ፓል | 891-866 ዓክልበ. | «የቱኩልቲ-ኒኑርታ ልጅ» |
3 ስልማናሶር | 866-831 ዓክልበ. | «የአሹርናሲርፓል ልጅ» |
5 ሻምሺ-አዳድ | 831-818 ዓክልበ. | «የስልማናሶር ልጅ» |
3 አዳድ-ኒራሪ | 818-790 ዓክልበ. | «የሻምሺ-አዳድ ልጅ» |
4 ስልማናሶር | 790-780 ዓክልበ. | «የአዳድ-ኒራሪ ልጅ» |
3 አሹር-ዳን | 780-762 ዓክልበ. | «የስልማናሶር ልጅ» |
5 አሹር-ኒራሪ | 762-753 ዓክልበ. | «የአዳድ-ኒራሪ ልጅ» |
3 ቴልጌልቴልፌልሶር | 753-735 ዓክልበ. | «የአሹር-ኒራሪ ልጅ» ቢባልም በመንፈቅለ መንግሥት የተነሣ ስሙም «ፑሉ» (ፎሐ) የተባለ ጦር አለቃ መሆኑ ስለሚታወቅ፣ ይህ አጠያያቂ ነው። |
5 ስልማናሶር | 735-730 ዓክልበ. | «የቴልጌልቴልፌልሶር ልጅ» |
2 ሳርጎን | 730-713 ዓክልበ. | |
ሰናክሬም | 713-689 ዓክልበ. | (በአሦርኛ ስሙ «ሲን-አሔ-ኤሪባ» ነበር።) |
አስራዶን | 689-677 ዓክልበ. | (በአሦርኛ ስሙ «አሹር-አሔ-ኢዲና» ነበር።) |
አስናፈር | 677-638 ግድም | (በአሦርኛ ስሙ «አሹር-ባኒ-አፕሊ» ነበር።) |
አሹር-ኤቲል-ኢላኒ | 638-634 ግ. | |
ሲን-ሱሙ-ሊሺር | 634 ዓክልበ. | |
ሲን-ሻር-ኢሽኩን | 634-620 ግ. | |
2 አሹር-ኡባሊት | 620-617 ዓክልበ. | በ620 ዓክልበ. ነነዌ በጦርነት ወድቆ መጨረሻ አሦራዊው ንጉሥ አሹር-ኡባሊት ከካራን ገዛ። |