የኡዝቤኪስታን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኡዝቤኪስታን እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1946 እ.ኤ.አ. ኡዝቤኪስታን በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ እያለች የተመሠረተ ሲሆን ከ1994 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የፊፋ እና የእስያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አባል ነው። ፌዴሬሽኑ የኡዝቤክ ሊግንና ሌሎችንም ብሔራዊ ውድድሮችን ያዘጋጃል። በተጨማሪም የኡዝቤኪስታን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።