የእንቦጭ አረም (Eichhornia crassipes) በጣም አስቸጋሪ የሆነ፣ በውሃ ላይ የሚበቅል ወራሪ አረም ነው።
በጣም ቶሎ ሊስፋፋ ይችላል። ይህ ማለት በየ፪ ሳምንት ውስጥ መጠኑ ሊደረብ ይችላል። ኩሬ ወይም ሃይቅ ሲሸፈን፣ ጸሓይን ወይም ሌሎችን አትክልት፣ አሦችን ይክለክላል፤ ለትንኝ እና ለብዙ ተላላፊ በሽቶች መኖሪያ ይሆናል። ከሌሎቹ በሽቶች በላይ አረሙ እከክ መፍጠር ይችላል።
በመጀመርያ ለደቡብ አሜሪካ ኗሪ ነበር። ዛሬ ግን ወደ ኒው ዚላንድ፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ፣ ካምቦዲያ፣ ሉዊዚያና ክፍላገር አሜሪካ፣ ኬረለ ክፍላገር ሕንድ፣ እና በቪክቶሪያ ሀይቅ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ማላዊና ግብጽ ወርሮ ትልቅ ችግር ሆኗል።
በእፃዊ ተዋልዶ በፍጥነት ማባዛት ስለሚችል፣ ትንንሽ ክፍሎች ቢሆኑም በውሃው ውስጥ ቢቀሩ፣ ዳግመኛ ውረት ሊሆን ይችላል።
በአንዳንድ አገር ውስጥ፣ እንቦጭን የሚበሉ የነቀዝ ዝርያዎች እና የብል፣ የፌንጣ ዝርያ እንዲበሉት አስገብተዋል።
ጉማሬ የእንቦጭ አረም እንዲበላ በማሠብ፣ በ1902 ዓም ጉማሬዎችን ወደ ሉዊዚያና ለማስገባት የሚል ሀሣብ በአሜሪካ ምክር ቤት ቀረበ፣ ሆኖም እንደ ሕግ መቸም አልተቀበለም።
አረሙ በበዛ ጊዜ አስቸጋሪ ሲሆን፣ አንዳንድ ጥቅሞ አለው።