የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፈረንሣይኛ፦ Fédération Camerounaise de Football) የካሜሩን እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። ፌዴሬሽኑ የተመሠረተው በ1959 እ.ኤ.አ. ሲሆን የካሜሩን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንንና የተለያዩ ብሔራዊ ውድድሮችን ያዘጋጃል።