የጣልያን ታሪክ

የኢትዮጵያ ታሪክ

ጣልያን (ኢትሊ፤ኢጣልያ፤ጣሊያን) በደቡባዊው አውሮፓ በተራራማ ሸለቆዎች ተከባ፣ ፖ ወንዝ ሸለቆ የሚባለውንም አቅፋ የቬኔሺያን ዝርግ ስፍራ ቦታ ጨምሮ ወጣ ብሎም የዳንዩብ የፍሳሽ መስመር እነ ላምፕዱሳ ደሴትንም ታካትታለች።

የጣልያን መንግስት ጣልያን የቡትስ ጫማ ቅርፅ ያላት ሀገር በመባልም፤ ከሮማ ፍርስራሾች፤ በህዳሴው ዘመን ውጤቶች ትታወቃለች። የሮሜ መንግሥት ዝና በዛሬው አለማችን ላያ በሰፊው ይታያል፤ ማለትም በህዝብ የተመረጠ መንግስት፤ በክርስትና፤ በላቲን አፃፃፍ ውስጥ ማለት ነው።

የጣልያን ዝርያዎች ላቲኖች Latins በመባል የሚታወቁት የሮማ ስርወ መንግስትን መሰረቱ ከሚጎራበቶቸውን እንደ ሴልትስ እና ሳባዊያን ያሉ ስልጣኔዎችን በመውረር እና በመጠቅለል ስለዚህም ጥንታዊውን የሮማውያን መንግስት መሰረቱ እናም ሮም ተፅእኖ ፈጣሪ እና ኀያል ሆና ብቅ አለች። ምንአልባትም ከ753 ዓክልበ.ቲበር ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተመሰረተችው ሮም ከብሪታኒያ እስከ ፐርሺያ ድረስ የግዛት ወሰን ነበራት። በአሁኑ ወቅት ጣልያን የአለማችን ቅርስ መዝገብ የሰፈሩ 51 የሚደነቁ ስፍራች ሲኗሯት በብዛትም ከሚጎበኙ አገሮች አንዲት ናት።

በአስራ አንድኛው ክ/ዘመን በባህር ዳርቻ ያሉ የመንግስት ይዞታዎች እነ ቬኒስ Venice; ፒዛ Pisa በተጋድሎም ከባይዛንቲን፤ ከአረቦች፤ ከኖርማን እንዲሁም በንግድ ፤በመርከብ አገልግሎት፤ በባንክ ግልጋሎት፤ ካፒታሊዝምን ከመጀመረም ጀምሮ በልፅገው ከሜዲትራኒአን እስከ የምስራቁ አለም ድረስ ያለውን የንግድ መስመር መቆጣጠር ችለው ነበር።

የጣልያን አስደናቂ የሕንጻ ጥበብ

ዘመነ ተህድሶ Renaissance(የሳይንስ፤ የስነ ጥበብ፤ የምርምር እና ሰውን ማዐከል ባደረገ ጥበብ) ጣልያን እና የተቀረው አውሮፓ ወደ ዘመናዊነት ገቡ። በዚህም ወቅት የጣልያን ባህል አበበ ። የባህል እና የጥበብ ብቅ ብቅ ማለት የህዳሴው ዘመን መሰረት ከጣልያን ነው ምክንያቱም በታዋቂዎቹ የንግድ ከተሞች በተገኘው ሀብት እና ተፅእኖ ባላቸው የቤተሰብ ስርዐት ጥበቃ ለምሳሌም የሜዲሲ ቤተሰብ እና በኮንስታንቲኖፖል መወረር ምክንያት ከግሪክ የፈለሱት ወይንም የተሰደዱት ምሁሮች ምክንያት ነው። ትላልቅ ከተሞች በመስፋፋት ሲኞሪ የተባሉ በነጋዴ ቤተሰብ የሚመሩ እና ክልላዊ ስረወ መንግስት ያላቸውን አስተዳደሮች መፍጠር ቻሉ።

የጥቁር ሞት ወረርሺኝ Black Death pandemic 1348 አንድ ሶስተኛውን የ ሀገሪቱን ህዝብ ጨርሶት የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ አልፎል ይሁንና የመልሶ መቋቋም ሂደት ለከተሞች ለንግድ እና ለኢኮኖሚው በረዳው ሂደት ለህዳሴው ዘመን ማበብ ረድቶል፡፡ ፍሎረንስሚላን፣ ቬኒስ Florence, Milan and Venice .

በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ማብቂያ ጀምሮ ኢጣልያ ሶማሊያ፤ ኤርትሪያን፤ ሊቢያ እና በአጌአን ባህር ላይ ያሉ ደሴቶችን  በቅኝ ገዢነት ወደ እራሶ አስተዳደር ጠቀለለች ይህም የምስራቅ አፍሪካ ዒጣሊያን ዓላማ ያነገበ ነበር፡፡

- ኤርትራ ጣልያን ፤ የጣልያን መንግስት በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉትን በ ስዊዝ መተላለፊያ መከፈት ምክንያት ብቅ ብቅ በማለት ያሉትን የንግድ መዳረሻዎች ከነጋዴ ባለቤቶቿ ላይ ገዛች (coaling station along the shipping lanes) ቀደም ብሎ የቀይ ባህር ዳርቻዎች በኦቶማን ቱርኮች አገዛዝ በግብጦች እይታ ስር የነበረ ቢሆንም (Khedivate of Egypt) በግብፆች እና በኢትዮጵያኖች በተደረገ ጦረነት ግብጦች በመሸነፋቸው አካባቢው ወደ አለመረጋጋት አመራ (Ethio-Egyptian War) ብሪቲሽ መንግስት ከግብፅ፤ ከኢትዮጵያ (British Hewett Treaty)፣ ከሱዳን ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እያጠኑ፣ ድጋፋቸውን ለኢጣሊ በመስጠታቸው ኢጣልያ ወደ ሰሜን እስከ ምፅዋ ድረስ ግዛቷን አስፋፋች፡፡

- ሶማሊያ ጣልያን፤ በ1888 የሶማሌ ቀነድ ሱልጣን ዩሱፍ አሊ ከንዲድSultanate of Hobyo እና ሌሎችም ከጣልያን ጋር በመዋዋል የጣልያንን ከለላ አገኙ ይሁን እና የጣልያን ፍላጎት በሱማሌ ወደቦች ላይ የስዊዝ መተላለፊያ እና የ ኤደን መግቢያዎችSuez Canal and the Gulf of Aden ላይ ትኩረት ነበር፡፡

- ሊብያ ጣልያን፤ ጣልያን በሰሜን አፍሪካ ግዛቷ የኦቶማን ተሪፖሊታና በኢታሎ ቱርክ Italo-Turkish War,ጦርነት ከወረረች በሆላ ኦቶማኖች ስልጣናቸውን ቢለቁም Treaty of Lausanne, ከ ሴኑሲ የሀይማታዊ እና የፖለቲካዊ ድርጅት ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው መሪያቸውም ኦማር አል ሙክታር Omar Al Mukhtar ነበር፡፡

- ኢትዮጵያ ጣሊያን፤ የኤርትራውን ግዛት ለማስፋት ጣልያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የግዛት ወሰን እና የመረዳዳት የውጫሌ ስምምነት በአተረጓገም ምክንያት ጣሰች Treaty of Wuchale with then Negus Menelik of Shewa በአደዋው ጦርነትም Battle of Adwa በመጋቢት 1896 የጣልያንው ቕኝ ገዢ ሀይል በኢትዮጵያኖቹ ለሸነፍ ችሏል፡፡

በ20ኛው ክፍለዘመን ከ1ኛው የዐለም ጦርነት ጊዜ ምንም እንኳን ጣልያን ከአሸናፊዎች አንዶ ብትሆንም የኢኮኖሚ እና የማህበረወዊ ውጥንቅጥ ውስጥ ገባች የሶቪዪቶችንም አይነት አብዮትም በመሸሽ በቤኒቶ ሞሶሎኒ የሚመራ ፋሺስት a Fascist አምባገነንነት አመራርበ 1922 ገባች፡፡ በ1935 ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በድጋሚ ወረር (Second Italo-Ethiopian War) በጦርነቱም ዘመናዊ በአየር ሀይል የታገዘ ብሎም በአለም አቀፍ ህግ የተከለከለ መርዛማ ጋዝ በመጠቀሙ በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ ውጤቱም ጣልያንን በጊዜው ከነበረው የመንግስታቱ ድርጅት ተገለለችLeague of Nations; Italy allied with Nazi Germany and the Empire of Japan. ይሑንና በወቅቱ ከነበረዉ አለምአቀፋዊ ሁኔታ አንፃር ጣልያን ላይ ማእቀቡ ተፅእኖ ሊፈጥር አልቻለም ቆይቶም ብዙ ሀገራት የህግ ጥሰቱን ችላ ብለውታል፡፡ ይህም ጊዜ ገፍቶ በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተባበሩት ወገን የሆነው ሲሲሊ በወረረ ጊዜ የፋሺስቱ አገዛዝ ተገረሰሰ ጣልያን በአገዛዛቸው ስር ብትወድቅም ጀርመኖች የሰሜን እና ማሀከለኛውን ጣልያን በመያዛቸው ጣልያን የጦርአውድማ ሆና ነበረች በዚም ጊዜ የፋሺስቱ አመራር ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት መሪው ሞሶሎኒም ተማረኮ ተገደለ ምንም እንኮን በብሪቲሽ ሶማሊላንድ እና በግብፅ ጣልያን እየገፋች የነበረ ቢሆንም ጣልያን በምስራቅ አፍሪካ በ ግሪክ በሩሲያ እና በ ሰሜን አፍሪካ ሽንፈት አጋጠማት፡፡

ጣልያን የተፃፈ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ህገ መንግስት በፋሺዝም ተቃራኒ ከሆኑ ተወካዮች ፤ለናዚ እና ፋሺስት መውደቅ፤ በሰሩ አባለት የተረቀቀ ህግ አላት ፤ የህግ ማስከበር ስራ በተለያዩ የፖሊስ አባላት (the Carabinieri are the gendarmerie and military police) ይከናወናል ለምሳሌ የጣልያን ብሄራዊ ፓርክ እና የደኖች ጥበቃ፤የመሰረተ ልማት አውታሮች ጥበቃ፤ ይሁንና የተደራጁ የወንጀል ድርጅቶች የማህበራዊ እና የፖለቲካ ስራዎችን ሲያዉኩ ይታወቀሉ ለዚህም  ማፊያ (Mafia) በሚባሉት ይታወቃሉ፡፡ 

የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስተር የሚኒስተሮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ነው ለዋና ውሳኔዎችም የእነሱን ፍቃድ ማግኘት አለበት፤ እናም ፓርላማውን የመበተን የሚደርስ ስልጣን የለውም፡፡

ሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል የኢንዱስትሪ ማዐከል በመሆኑ ደቡብ እና ገጠራማው ክፍልም ያልበለፀገ በመሆኑ ለጠቅላላ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድክመት ምክንያት ነው ፤ ምንም እንኮን ጣልያን የተለያዩ ዲያልክት ቢኖሩም ብሄራዊ የሆነ የትምህርት ስርአት በመኖሩ የተለያዩ የቋንቋ ንግግሮች በሀገሪቱ እንዳይኖር አድርጓል ብሎም የመገናኛ ስርጭት መስፋፋት እና የኢኮኖሚው ማደግ ተከትሎ አንድ ወጥ ስርአት መጠቀም ቻሉ፡፡ የትምህርት ደረጃ በመጀመሪያ(ጣልያንንኛ፤ እንግሊዘኛ፤ ታሪክ የመሳሰሉትን አካቶ 8 አመታትን ይወስዳል ) በሁለተኛ( 5 አመታትን እና የባህል ትምህርት ቤቶችን ያጠቃልላል) በሶስተኛ( በህዝብ፤ በግል ፣ እና በተመረጡ ከፍተኛ ኒቨርስቲዎች ) ተከፋፍሎ ሊሲኦ የሚባለው ፈተና ተማሪዎችን ለዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ይረዳቸዋል፤ ይሁንና የጣልያን የትምህርት ስርአት ከቀረው አውሮፓ ጋር ሲወዳደር ደረጃው ዝቅተኛ ነው፡፡

ጣልያን ስለ ሚደነቁቁ እና ስለ ሚታወቁ የስነ ህንፃ ክህሎቶች ትታወቃለች ለምሳሌ ያህል ኮሎሰም  Colosseum፤ ሚላን ካቴህድራል፤ የተንጋደዱት የፒዛ ማማዎች Leaning Tower of Pisa  እና የቬኒስ ከተማ ግንባታ እናም አርክ ዶምስ በመባል የሚታውቁትንም የስነ ህንፃ ዲዛይኖች እናም የልኡል ቤተሰቦች በአብዛኛውም ከ እንግሊዝ እና ሌላውም አለማት በዲዛይናቸው ተደንቀው መኖሪያ ቤታቸውን እና ቤተመንግስታቸውንም አስመስለው ሰርተዋል፡፡  

የጣልያን ገበታ በአብዛኛው በባህላዊ ውጤቶች Cheese, cold cuts and wine ላይ በማተኮሩ ይፈለጋል ፤ቡና፣ እስፕሬሶ፣ ቴራሚሱ ፣ካሳታ፣. Pizza Margherita, spaghetti alla carbonara, espresso and gelato.ፒዛ፣ ፓስታ፣ ጄላቶ፣ ከሚታወቁት መካከል ናቸው፡፡

Flag of Italy.svg
Flag of Italy

[[File:Italian food.JPG|thumb|Italian cuisine (clockwise): Pizza Margherita, spaghetti alla carbonara, espresso and gelato.]]

Italian food

የጣልያን ተወዳጅ እስፖርት የእግር ኮስ ጨዋታ soccer,ነው  ብሄራዊ ቡድኑም  ሰሚያዊዎቹ(nicknamed Gli Azzurri – "the Blues")  በመባል ይታወቃሉ፤ ከፍተኛው የእግርኮስ የጨዋታ ፕሮግራም ሴሪአ  ከ አውሮፓ በተመራጭነት 4ኛ ነው፡፡ የፊፋና ዋንጫ አራት ጊዜ በማንሳት ጀርመን እና ብራዚልንም ትከተላለች (1934, 1938, 1982, and 2006). ሮቤርቶ ባጂዮ ከጣልያን ነው: [roˈbɛrtoˈbaddʒo]     ,    ::https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/2/21/Italia82.JPG/360px-Italia82.JPG
የጣልያን ሲኒማ  ታሪክ ከ ሉሚር ወንድማቾች the Lumière brothers  የተንቀሳቃ ሽፊልሞች ተእይንት   ካሳዩ በሆላ ይጀምራል፤ የታላቁ ዉበት ፤ህይወት ቆንጆ ነው፤  ፖስተኛው፤ ጥሩው መጥፎው እና አስቀያሚውThe Good, the Bad and the Ugly and Bicycle Thieves የባይስክሉ ሌቦች ፤የመሳሰሉት  ከሲኒማ መህደሮች ታዋቂዎቹ ናቸው፡፡


ዋኖዎቹ የጣልያን የፋሽን አይነቶች ፣ጉሲ ፤ ፕራዳ Gucci, Armani, Prada, Versace, Valentino፣ እንደ እንግሊዝ እን ሰሜን አሜሪካ ታዋቂ ናቸው፡፡ የጣልያን ቃላቶች እንደ("Bel Disegno" and "Linea Italiana") የእነጨት ውጤቶች (furniture) መዝበ ቃላት ውስጥ ገብተውላታል፡፡ ሌሎችም ታዋቂ የጣልያን ዲዣይኖችም ፈሪጅ፤ ሶፋ Zanussi's washing machines ፣ fridges፣ sofas ናቸው፡፡

የአዲሲቷ ጣልያን ቋንቋ መሰረቱ በ ፈሎሬንቲን ገጣሚ ዳንቴ አሊገሂሪDante Alighieri ተጥሎል የሱም የተደነቀ ኮመዲ(አስቂ) በአውሮፓ ውስጥ ከነበሩ የስነፅሁፍ ስራዎች ዝናኛው ነው፡፡  በኢጣልያ  የስነፅሁፍ ሰው ለመጥቀስ አይቸግርም እነ አሌሳንድሮ ማንዞኒ፤ ጂዮቫኒ ቦካሲዮ፤ በዚህም እንደ ሶኔት ያሉ የግጥም ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡ የሮማ ድራማቲስቶች ከግሪክ  ተውኔቶችን ተቀድተው ተተርጉመው ተሰርተዋል ፤ የካርሎ ኮሎዲ ድርሰት  የፒኖቼ አጋጣሚ ፤ ታዋቂ የልጆች ደርሰት ነው Carlo Collodi's 1883 novel, The Adventures of Pinocchio. ፡፡
የጣልያን ቋንቋ ጂኦግራፊያዊ ስብጥር

ፒያኖ፤ ቫዮሊን በኢጣልያ ነበር የተገኙት፤ ሉቺያኖ ፓቫሮቲምLuciano Pavarotti, ከጣልያን ነው፡፡

የንፅፅር ዕይታን በመጠቀም የስዕልን እና የቅብ ውጤት ወደ ላቅ ያለ ደረጃ የደረሱት እነ ሚካኤል አንጄሎ ፣ራፋኤል Michelangelo, Raphael, Botticelli, Leonardo da Vinci, and Titian ሲሆን፤ የሰው ዐካላትን study of human anatomyእና የመጠን ልዩነታቸውን የሚያጠናውን ሳይንስም ትምህርት ክፍልም ከጣልያን ነው የተገኘው፤ እናም እንደ ሊኦናርዶ ዳ ቪነች as Leonardo da Vinci፤ ጋሊልኦGalileo  የዘመናዊው ሳይንስ እና የስነ ህዋ አባት፤ ክ.ኮሎምበስ ተጓዡ Christopher Columbus፤የፊዚስት ሊቁ  ኤነሪኮ ፈረሚ  Enrico Fermi; በ ሂሳብ ላግራንጄ , Joseph Louis Lagrange ፤ በሂሳብ አያያዝ ወይንም አካውንቲንግ  (double-entry bookkeeping system for tracking credits and debits.. Luca Pacioli  ) ፤በኬሚስትሪ አ. አቮጋርዶAmedeo Avogadro የመሳሰሉ የጥበብ ሰዎችን መገኘት  መጥቀስ ይቻላል፡[1]
  1. ^ https://en.wikipedia.org/wiki/Second_Italo-Abyssinian_War https://en.wikipedia.org/wiki/Italian_Libya https://en.wikipedia.org/wiki/Italian_Somaliland https://en.wikipedia.org/wiki/Italian_Eritrea https://en.wikipedia.org/wiki/Battle_of_Adwa http://europe-cities.com/destinations/italy/culture/ Archived ጁን 8, 2017 at the Wayback Machine