ያኑስ

ያኑስ (ሮማይስጥJanus) በሮሜ አረመኔ ሃይማኖት ውስጥ ጣኦት ወይም አምላክ ነበረ። የወሩ ስም ጃንዩዌሪ የመጣ ከሱ ነው።

በሮማውያን ትውፊቶች ዘንድ ያኑስ መጀመርያ በጣልያን (ላቲዩም) ይነግሥ ነበር፤ መንግሥቱንም ከሳቱርን ወይም ካሜሴ ጋር ይይዝ ነበር። ከዚህ በላይ የጄኖቫያኒኩሉም ከተሞች መስራች እንደ ነበር የሚል ልማድ አለ።

ማርቲን ዘኦፓቫ (1240 ዓ.ም. ገደማ)፣ የሚራቢሊያ ዑርቢስ ሮማይ ኋለኛ ቅጂዎች፣ እና የጆቫኒ ዲ ማሪንዮላ ክሮኒኮን ቦሄሞሩም (1347 ዓ.ም.) ሁላቸው ሲስማሙ፣ ወደ ጣልያን አገር ፈልሶ ሥነ ፈለክን ፈጥሮ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ያኑስ ነበረ።

ጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ (1490 ዓ.ም. የታተመ)፣ ያኑስ የኖኅ ልጅ ሳይሆን የኖኅ እራሱ ሌላ ስም ነው። ኖኅ በአራራት ላይ ወይንን ስለ ተከለ፣ የስሙ «ያኑስ» ትርጉም በአራማይስጥ «ወይን» እንደሆነ ይላል። ከናምሩድ መንግሥት ቀጥሎ ያኑስ ከተሞችና ሠፈረኞች እየተከለ በዓለሙ ይዛወር ነበር። በመጨረሻ ያኑስ ካምን ከጣልያን አባርሮ መንግሥቱን ያዘ። በዚህ አቆጣጠር በጣልያን ሀገር የነገሠ ከ2292 እስከ 2211 ዓክልበ. ግድም ነበር።

ቀዳሚው
ካም «ኤሴኑስ»
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
2292-2211 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ክራኑስ ራዜኑስ

ዋቢ መጽሐፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]