ይታይሽ «ቲቲ» አየነው (1992 እ.ኤ.አ. ተወለደች) በእስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ እስራኤላዊት ሆና ወይዘሪት እስራኤል የሆነች ወጣት ናት።[1] በወይዘሪት ዓለም የውበት ውድድርም ላይ እስራኤልን ወክላ ትሳተፋለች።[1]
ይታይሽ በChahawit ሠፈር፣ ጎንደር አካባቢ ነው የተወለደችው።[2] እናትና አባቷ ልጅ እያለች ሞተዋል። ይታይሽ በ፲፪ ዓመቷ ከአያቶቿ ጋራ ወደ እስራኤል አመራች። የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ በእስራኤል የመከላከያ ኃይል ውስጥ በመቶ አለቃነት (Lieutenant) አገልግላለች።[3] ከዚያም በአልባሳት መደብር ውስጥ ሠርታለች።[2]
በማርች 2013 እ.ኤ.አ.፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እስራኤልን በጎበኙ ጊዜ ይታይሽ ከአሜሪካኑ ፕሬዚዳንትና ከእስራኤል ፕሬዚዳንት ሺምኦን ፔሬስ ጋር እራት ተጋብዛለች።[4]