ዮሐንስ ፬ኛ

==

ዓፄ ዮሐንስ 4ኛ
ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ከልጃቸው ከራስ አርአያ ሥላሴ ጋር
ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ከልጃቸው ከራስ አርአያ ሥላሴ ጋር
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከጥር ፲፫ ቀን ፲፰፻፷፬ ዓ.ም. እስከ መጋቢት ፪ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ.ም.
በዓለ ንግሥ ጥር ፲፫ ቀን ፲፰፻፷፬ ዓ.ም.
ቀዳሚ ዳግማዊ ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ
ተከታይ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ
ልጆች ራስ አርአያ ሥላሴ
ራስ መንገሻ
ሙሉ ስም አባ በዝብዝ (የግብር ስም)
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን፣ የትግራይ ቅርንጫፍ
አባት ደጃዝማች መርጫ
እናት ወ/ሮ ሥላስ
የተወለዱት ሐምሌ ፭ ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. በተንቤንትግራይ
የሞቱት መጋቢት ፪ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ.ም.
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና

==


ዓፄ ዮሐንስ 4ኛ፣ ከአባታቸው ከተንቤን ባላባት የራስ ስኹል ሚካኤል የልጅ ልጅ ሹም ተንቤን ምርጫ እና ከናታቸው የእንደርታው ገዢ የራስ አርአያ እህት ወይዘሮ ወለተ ሥላሴ ሐምሌ 5 ቀን 1829 ዓ.ም. ማይ በሀ በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።

ርዕሰ መኳንንት ደጃዝማች በዝብዝ ካሳ ሐምሌ ፮ ቀን 1863 ዓ/ም ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስአድዋ አካባቢ አሳም የሚባል ሥፍራ ላይ ወግተው ድል ካደረጉ በኋላ ጥር 13 ቀን1864 ዓ/ም አክሱም ላይ ሥርዓተ ንግሣቸው ተፈጽሞ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ።

አፄ ዮሐንስ 4ኛ ከእንግሊዝ ንግስት ጋር በመፃፃፍ ነግስናቸውን አጠናክረዋል፡፡ ይህም ተቀናቃኛቸው የነበሩት አፄ ሚኒለክን ለማስገበር ተሳክቶላቸዋል ፡፡ ከአፃ ሚኒሊክ ጋር የነበራቸውን የስልጣን ሽሚያ ለመከላከል ሲባል ደብረ ብርሃን ድረስ በመሄድ ድርድር በማድረግ የነበራቸውን ባላንጣነት አስወግደው ሚኒሊክ ንጉስ እንድባልና አፄ የሐንስ ርዕሰ ብሔር እንድሆን ተስማምተዋል ፡፡ ከዛም ደርቡሾች ጋር መተማ አካባቢ ገጥመው አፄ ዮሐንስ በጥይት ቆስለው መውደቃቸው ይነገራል፡፡ ይህ የሆነው ደርብሾች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነው የጎንደርና ኣካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ስላካሄዱ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አፄ ዮሐንስ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ለሃገራቸው በድንበር ላይ ሲዋጉ የሞቱ ብቸኛው ንጉሰ ነገስት ያረጋቸዋል። ከዚህ በፊትም ከግብፅፆች ጋር ጉራና ጉንዳ ጉንድ በተባሉ ቦታዎች ገጥመው ማሸነፋቸውና የሀገርን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ መጣጣራቸን በታሪክ ይወሳል፡፡

  • (እንግሊዝኛ) Zewde, Bahru, "A History of Modern Ethiopia 1855-1991, AA University Press (2001)
  • መሪ ራስ አማን በላይ "የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ" (1985 ዓ/ም)


አፄ ዮሃንስ 4 በወሎ አካባቢ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ ብቻ ነው ወይስ በሁሉም ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ላይ አደጋ አድርሰዋል? የአደጋው መጠንና ሁኔታ ቢብራራ ጥሩ ነው፡፡

8