ደደሆ (Euclea racemosa) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ሁሌ ለም ዛፍ ወይም ቊጥቋጥ አይነት ነው። ብዙ ቅጠላቅጠልና ትንንሽ ቀይ፣ ሐምራዊና ጥቁር ፍሬዎች አሉበት።
በአፋርኛና በሶማልኛ የሌላ ዝርያ ዛፍ Salvadora persica «ደደሆ» ይባላል፤ የዚያው ዛፍ ስም በአማርኛ መሮ ነው።
በኮረብቶች ወይም በእዳሪ መሬት ተራ ነው።
በምስራቃዊው አፍሪካ ከግብጽ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ፣ እንዲሁም በኮሞሮስ፣ በኦማንና በየመን ይገኛል።
ትንንሽ ፈሬዎቹ ሊበሉ ይቻላል፤ በትልቅ መጠን ቢበላ ግን የሆድ ማበጥ ያደርጋል። ፍሬዎቹም በአዕዋፍ ይበላሉ።
ፍሬዎቹም «የደደሆ ኮምጣጤ» ለመሥራት ይጠቀማሉ።
ጥቁር ፍሬዎቹ ደግሞ ሐምራዊ ቀለም ለመሥራት ይጠቀማሉ።[1]
በፍቼ በተደረገ ጥናት ዘንድ፣ የደደሆ ቅጠል ዱቄት ለጥፍ ለኪንታሮት ይለጠፋል። የቅጠሉ ጭማቂም ለኮሶ ትል ወይንም ለአባለዘር በሽታ ይጠጣል። አገዳውም ለጥርስ ሕመም ይኘካል።[2]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |