የኮሉምቢያ ቀጠና የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (እንግሊዝኛ: District of Columbia Public Schools (DCPS)) አሜሪካ ውስጥ በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የሕዝብ ትምህርት ቤት ሥርዓት ነው[1]።
ዲሲፒኤስ በጠቅላላው የ168 ትምህርት ቤቶች እና የመማርያ ማዕከሎች ስብስብ ሲሆን፤ 101 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 11 መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 9 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 20 የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አሉት። በተጨማሪም በዚህ ሥርዓት ውስጥ 6 የትምህርት ማዕከሎች እና 20 ልዩ ትምህርት ቤቶች ተካተዋል። በ2003 እ.አ.አ. ሥርዓቱ በአጠቃላይ 65,099 ተማሪዎች ነበሩት።