ድግጣ ወይም ዝግጣ (Calpurnia aurea) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ዘሩ በማር ለጥፍ ለተስቦ መጠቀሙ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ተዘገበ። እንዲህ ያለ ለጥፍ ከክትክታ ዘር ጭምር ለተስቦ ሊሰጥ ይችላል። አንድ ሌላ ዝግጅት ለሆድ ትል፣ ለብርቱ ተቅማጥ ወይም ለአንገት ነቀርሳ ይሰጣል፦ የድግጣ እና የክትክታ ቅጠል፣ የምድር እምቧይና የሉት ሥር፣ የቁልቋልና የቅንጭብ ላፒስ፣ ተደቅቀው በውሃ ይጠጣል።[1]
በፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ ቅጠል፣ ፍሬውና ዘሩ በምግብ ውስጥ ለውሾች ውሻ በሽታ ለማከም ይሰጣል። የድግጣ ቅጠል ተደቅቆ በውሃ ለልክፈት ወይም ለቁስል ይለጠፋል። ፍሬውም ተደቅቆ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[2]
በዘጌ እንደ ተዘገበ፣ የፍሬው ወይም የቅጠል ዱቄት በማር ወይም በውሃ ለቁርባ ለማከም ይጠጣል።[3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |