ዶክቶር ሁ (በእንግሊዝኛ: Doctor Who) የእንግሊዝ ቢ.ቢ.ሲ. ሳይ-ፋይ ቴሌቭዥን ድራማ ነው።
ዶክቶሩም ከውጭ አለም (ከሌላ ኮከብ) የመጣ፣ በጠፈር ብቻ ሳይሆን በጊዜ በኩል ከአንዱ ወቅት ወደ ሌላው ወቅት መጓዝ የሚችል ዝርያ ነው።
ከ1963 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ 13 ተዋንያን የዶክቶሩን ሚና አጫውተዋል። የ «መጀመርያው ዶክቶር» ክፍሎች (እስከ "The Chase" ድረስ) በኢትዮጵያ ከ1970 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ድረስ በ ETV ይታዩ ነበር። ከነዚህም ክፍሎች መካከል ሦስቱ "Marco Polo", "Reign of Terror" እና "the Crusade" በማናቸውም አገር በኢንግላንድ ቢሆንም ምንም ቅጂ ሳይገኝላቸው የማይተርፉ ተብለዋል።[1]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |