ጂራን | |
ጂራን ከተማ በ1878 ዓ.ም. | |
ጂራን ከጅማ በስተሰሜን ምስራቅ 5ኪሎሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። የተቆረቆረችውም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በኦሮሞ መሪ አባ መጃል ነበር። አባ መጃል አባ ጅፋር ተብሎ የሚታወቀው የጅማ ግዛት መስራች ናቸው። ከተማይቱ ከፍተኛ እድገት ያሳየው በልጃቸው በቀዳምዊ አባ ጅፋር (መሐመድ ዳውድ) ዘመን ነበር። በወቅቱ የጅማ ግዛት ዋና ከተማ የነበረች ሲሆን ለዚህ እድገቷ ዋና ምክንያት በሸዋ እና ከፋ የንግድ መንገድ ላይ መገኘቷ ነበር፡ ከተማይቱ ብዙ አይነት ብሐረሰቦችንና ከእሩቅ አገር የሚመጡ ነጋዴወችን (ለምሳሌ ጎጃም) ሳይቀር ታስተናግድ እንደነበር ታሪክ አጥኝው ዶናልድ ሌቪን ዘግቦት ይገኛል[1]።