ገሱባ Gasuubba Ambbaa | |
ከተማ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ከንቲባ | ተስፋዬ ሀንጣሎ |
ከፍታ | 1,549 ሜ. |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 13,927 |
ገሱባ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ከተማ ሲሆን የሚገኘው በወላይታ ዞን ነው። ከሶዶ ከተማ ያለው ግምታዊ ርቀት ወደ ደቡብ ምዕራብ 33 ኪሎ ሜትር ያህል ነው። እንዲሁም ከአዲስ አበባ እስከ ገሱባ ያለው ርቀት 352 ኪሎ ሜትር በቡታጅራ-ሶዶ በኩል ወደ በስተደቡብ በኩል ይገኛል። ገሱባ ከተማ የኦፋ ወረዳ አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና ታገለግላለች። ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ በ1,549 ሜትር ላይ ትገኛለች። በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ከሚገኙት ስድስት ከተማ መስተዳደር ከተሞች መካከል ገሱባ ከተማ አንዱ ነው። ከ30,000 በላይ ህዝብ ያላት ከተማ ሲሆን ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሏት። በከተማዋ ያሉት አገልግሎቶች የ24 ሰአት የኤሌክትሪክ መብራት፣ የንፁህ ውሃ አገልግሎት፣ አፀደ ህጻናት፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያ፣ የእለት ተእለት የህዝብ ገበያ እና ሌሎችም ናቸው። ገሱባ በ6°43'27"N 37°33'24"ኢ መካከል ትገኛለች።
ገሱባ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ብዙ ህዝብ ተጠጋግተው ከሚኖርባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። በ2018 የኢትዮጵያ የማዕከላዊ ስታቲስቲካዊ ኤጀንሲ የህዝብ ቁጥር ትንበያ መሰረት፣ ገሱባ ከተማዋ በድምሩ 13,927 ሕዝብ አላት:: ከእነዚህም መካከል ወንዶች 6,870 እና ሴቶች 7,057 ናቸው።[1]
|