ጉኑኖ

ጉኑኖ
Gununo Ambbaa
ከተማ
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ዞን ወላይታ
ወረዳ ዳሞት ሶሬ
ካንቲባ ወንድሙ ደረጀ
ጉኑኖ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ጉኑኖ
የጉኑኖ ፡ አቀማመጥ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ

6°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°38′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ጉኑኖ በኢትዮጵያ ወላይታ ውስጥ ያለ ከተማ ነው። ከተማው በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ የአስተዳደር ዋና ከተማ ሆኖ ያገለግላል። ጉኑኖ የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከሆነችው ከአዲስ አበባ በ345 ኪሎ ሜትር እና ከወላይታ ዞን ዋና ከተማ ሶዶ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በጉኑኖ አቅራቢያ የሚገኙት ሌሎች ወረዳዎች; በደቡብ በሶዶ ዙሪያ፣ በሰሜን ምዕራብ በቦሎሶ ቦምቤ፣ በምዕራብ በኪንዶ ኮይሻ፣ እና በምስራቅ በቦሎሶ ሶሬ። የጉኑኖ ከተማ በካርታ ላይ የሚገኘው 6°55'21"ሰሜን 37°38'57"ምስራቅ ነው።

የህዝብ ቁጥር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ2020 ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባደረገው ትምቢያ መሰረት የጉኑኖ አጠቃላይ ህዝብ ብዛት 15,700 ነው። ከዚህ ውስጥ 7,963 ወንዶች ሲሆኑ 7,737 ደሞ ሴቶች ናቸው።[1] በዚህ ከተማ ውስጥ ያሉ የሴቶች የመራቢያ ዕድሜ ቡድን ወደ 23.3% ወይም በቁጥር 6,360 ገደማ ነው። በከተማው ውስጥ አንድ ጤና ጣቢያ እና ሶስት የግል ክሊኒኮች ብቻ አሉ።

  1. ^ "የጉኑኖ ከተማ ህዝብ ቁጥር". Archived from the original on 2022-07-07. በ2022-02-04 የተወሰደ.