ጉግል ዜና (Google News) በኮምፒዩተር ዜናዎችን የሚያቀርብ አገልግሎት ነው። ባለቤቱ ጉግል ድርጅት ነው። የዜና ዌብሣይቱ በአፕሪል 2002 እ.ኤ.አ. የቤታ ለቀቃ ሆኖ ነው የወጣው። በዌብሳይቱ የሚቀርቡት ዜናዎች እንዳሉ በኮምፕዩተር የሚመረጡ እና የሚደራጁ ሲሆን ምንም አይነት የሰው ግንኙነት የለም። አገልግሎቱ በአንድ ቋንቋ ውስጥ በ30 ቀናት ውስጥ የወጡ ዜናዎችን ያቀርባል። በእንግሊዝኛው ዕትም ውስጥ 4,500 የዜና ምንጮች አሉ።
ጉግል ዜና የፍለጋ አገልግሎት ሲኖረው ውጤቶቹንም በቀንና በሰዓት መመደብ ይቻላል።