ጡንቻ በባለሰውነቱ የመወጠር ወይም የመኮማተር ትዕዛዝን ሊቀበል የሚችል የስጋ ክፍል ነው። የጡንቻ ህዋሳት ለመኮማተር እና ለመወጠር የሚያስችሉ መዋቅሮች አሏቸው። እነዚህ መዋቅሮች በመኮማተር እና በመለጠጥ የህዋሱን ቅርፅ ይለዋውጡታል።