| ||||
---|---|---|---|---|
ጢያ | ||||
የጢያ ደንጊያ ሃውልቶች | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | ባሕላዊ | |||
መመዘኛ | c(i)(iv) | |||
የውጭ ማጣቀሻ | 12 | |||
አካባቢ** | አፍሪካ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርስ የሆነበት ጊዜ | 1972 (4ኛ ጉባኤ) | |||
* በዩ.ኔ.ስ.ኮ ስሙ እንደሰፈረ። ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
ጢያ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው። በጉራጌ ዞን ስር ሲመደብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይገኛል።
ጢያ የሚታወቀው ከአጠቅገቡ በሚገኘው ታሪካዊ ቅርስ ነው። በዚህ ቦታ 36 እራሳቸውን ችለው የቆሙ የደንጊያ ሃውልቶች ሲገኙ፣ 32ቱ ትርጉማቸው በውል የማይታውቅ ቅርጻ ቅርጾች፣ እንደ ጎራዴ ምስል ያሉ በላያቸው ላይ ሰፍረውባቸው ይገኛሉ። እንዳንድ ተማሪዎች አገላለጽ እኒህ ቦታወች የመቃብር ቦታ ነበሩ [1] ። የጀርመን ብሔር አጥኝዎች እኒህን ሃውልቶች በ1927 እንዳጠኑ ይዘገባል[2]። ከ1972ዓ.ም. ጀምሮ አካባቢው በዩኔስኮ የአለም ቅርስ ተደርጎ ተመድቧል።
ሌሎች ከጢያ አጠገብ የሚገኙ መስህቦች መልካ አዋሽና ሔራ ሸጣን እና አገሶቄ ይጠቀሳሉ።
እንደ 1997 የህዝብ ቆጠራ፣ ጢያ ውስጥ 3፣363 ሰዎች ይኖሩ ነበር [3]።