ጥንጁት (otostegia integrifolia) በኢትዮጵያና በየመን ብቻ የሚበቅል እጽ ሲሆን ብዙ ጥቅም አለው። ባብዛኛው ግን የመጠጥ እቃዎችን እንደ ጋን እና ገምቦ ያሉትን ለማጠን የሚያገለግል ነው።
ልብስም ለማጠን፣ በአንድም ሥነ ስርዓት እናትን በወለደችው በዐሥረኛው ቀን ለማጠን ያገልግላል።[1]
ጢሱም ለሳንባ ነቀርሳ ወይም ለማስታወክ በባህላዊ ሕክምና ተዝግቧል።[2]
የጥንጁት ቅጠል ጭማቂ በውሃ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለመጋኛ ለማከም ሊጠጣ ይችላል።
ለትኩሳት («ምች»)፣ የጥንጁትና የዳማ ከሴ ቅጠልና አገዶች፣ እንደ ጢስ መተንፈስ ያከማል። ወይም ደግሞ የጥንጁትና የዳማ ከሴ ቅጠላና አገዶች፣ የብሳናና የነጭ ባሕር ዛፍ ቅጠል፣ እና የፌጦ ዘር በውሃ ተፈልተው እንፋሎቱን መተንፈስ ለ«ምች» ያከማል።[3]
በኮረብቶች፣ በተወ መሬት፣ በስሜን ኢትዮጵያ (በጌምድር፣ ትግራይ) ተራ ቊጥቋጥ ነው።