ጸጉራም ድመት-ጥፍር (Uncaria tomentosa) ደቡብ አሜሪካና መካከለኛ አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ ሐረግ ተክል ነው። በተለይ በአማዞን ወንዝ ሸለቆ ይገኛል።
እንደ ሜንጦ ወይም እንደ ጥፍር የሆኑት እሾሆች ስላሉበት በዛፍ ላይ ይወጣል።
ጸጉራም ድመት-ጥፍር በተለይ በኮስታ ሪካ፣ ኒካራጓ፣ ፓናማ፣ ቬኔዙዌላ፣ ኮሎምቢያ፣ ትሪኒዳድና ቶቤጎ፣ ኤኳዶር፣ ፔሩ፣ ሱሪናም፣ ጋያና፣ ጊያን ይገኛል።
ጸጉራም ድመት-ጥፍር በደቡብ አሜሪካ ባሕላዊ ሕክምና ለተለያዩ ህመሞች ጥቅም አገኝቷል። በቀቿ ቋንቋ ሐረጉ «ቪልካ ቆራ» ወይም «ቅዱስ ዕጽ» ተብሏል።