ፊሊፕ ጆንሰን (ከጁላይ 6፣ 1906 እስከ ጃንዋሪ 25፣ 2005 እ.ኤ.አ. የኖረ) አሜሪካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሕንፃ ጥበበኛ (አርኪቴክት) ነበር። በ1930 እ.አ.አ. በኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የዘመናዊ ጥበብ ሙዚየም (Museum of Modern Art) ውስጥ የአርኪቴክቸር እና ዲዛይን ክፍልን (Department of Architecture and Design) አቋቋመ። በኋላም (በ1978 እ.ኤ.አ.) ከአሜሪካ የአርኪቴክቶች ተቋም የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም (በ1979 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የPritzker Architecture Prize ሽልማት አገኘ። ፊሊፕ ጆንሰን በሃርቫርድ የዲዛይን ትምህርት ቤት ነበር የተማረው።