ፋሌቅ

ፋሌቅ በ1545 ዓ.ም. ለሳለው ለጊዮም ሩዊ እንደ መሰለው

ፋሌቅ (ዕብራይስጥ፦ פֶּלֶג /ፔሌግ/) በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የዔቦር ልጅና የራግው አባት ነበረ።

ዘፍጥረት 11፡18-19 ስለ ፋሌቅ እንደሚለው፣ የፋሌቅ ዕድሜ 130 ዓመት ሲሆን ራግውን ወለደ፣ ከዚያም ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ። እነዚህ ቁጥሮች ከግሪኩ ትርጉም ሲገኙ የዕብራይስጥና ሳምራዊው ትርጉም ቁጥሮች ግን ይለያያሉ። በእብራይስጥ ትርጉም በ30 ዓመት ራግውን ወለደ፣ ከዚያም 209 ዓመት ኖረ፤ በሳምራዊውም በ130 ዓመት ራግውን ወለደ፣ ከዚያም 109 ዓመት ኖረ። በተጨማሪ በዘፍጥረት 10፡25 ዘንድ በፋሌቅ ዘመን ምድሪቱ ተከፍላለች። ይህ የሴምካምያፌት ልጆች ኩፋሌ እንደ ሆነ ይታመናል።

መጽሐፈ ኩፋሌ 8፡40 ፋሌቅ ከአባቱ ኤቦርና ከእናቱ አዙራድ በ1567 አመተ አለም ተወለደ። የምድር አከፋፈል በ1569 አ.አ. ሆነ (9፡1)። በ1577 አ.አ. ፋሌቅ ሚስቱን ሎምና አገባ፤ እርሷም የሰናዖር ልጅ ትባላለች። በ1580 አ.አ. አዙራድ ልጁን ራግውን ወለደችለት; የባቢሎን ግንብ በ1596 አ.አ. ተጀመረ ይላል (10፡10-11)።