ፓርጋ

የፓርጋ ሥፍራ በግሪክ አገር

ፓርጋ (ግሪክ፦ Πάργα) በስሜን-ምዕራብ ግሪክ ያለው መንደር ነው። የሕዝቡ ብዛት 4000 ያሕል ሰዎች ነው። ፓርጋ አንድ ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ፖስታ ቤትና ወደብ አለው።

በጥንታዊ ግሪክ ስሙ 'ሂውፓርጎስ' ተብሎ ነበር። በ1562 ዓ.ም. የቬኒስ ሰዎች ከመንደሩ ወደ ስሜን አምባ ሠሩ።